አየለ ማሞ (ማንዶሊን) በቀን አንድ ግጥም ወይም ዜማ ሳይሰራ ውሎ አያድርም፡፡

‹ግጥምና ዜማ አለህ?›

‹ሞልቶኛል›

80ኛ ዓመቱን  ይዟል፤ እሱ እንደሚናገረው የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ከወጣቶች ጋር መዋሉ ወጣት መስሎ እንዲታይ አድርጎታል፡፡ሰዎችም እንቅስቃሴው የወጣት ስለሚመስላቸው ‹እርሱ ዘወትር ወጣት ነው!› ይላሉ፡፡

በመሠረቱ ለእርሱ ወጣት መስሎ መታየት ልዩ ምስጢር የለውም፡፡ ሥጋ ያስረጃል ቢባልም አየለ ግን የስጋ ነገር አይሆንለትም፡፡ ከልጅነት ዘመኑ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ  ያልተበረዘና ያልተከለሰ የማር ጠጅ  አፈላልጎም ቢሆን ይጠጣል፡፡ወጣት የመምሰሉ ምክንያት ይገለፅ ከተባለ ከእግዚአብሔር ቸርነት ጋር ከስጋና ከማር ያልተለየ መሆኑ እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ዳሩ ግን እርጅና ከነጓዙ እየመጣ መሆኑን ያስባል፡፡

አየለ ከአንጋፋ የግጥምና ዜማ ደራሲያም መሀከል አንዱ ነው፡፡ 56 ዓመታት በሙዚቃ ውስጥ ኖሯል፡፡በእርሱ የተደረሱ ግጥም ና ዜማዎችን ጥላሁን ገሠሠ፤ማህሙድ አህመድ፤ ኩኩ ሰብስቤ፤ሀመልማል አባተ፤ህብስት ጥሩነህ፤ኤፍሬም ታምሩ፤ብዙነሽ በቀለ፤፣ለብፅአት ስዩም ፣ ለወረታው ውበት ፣ ለአስቴር ከበደ ፣ለ እያዩ ማንያዘዋል ፣ ሻምበል በላይነህ፣ ደረጀ ደገፋው ፣ጌታቸው ጋዲሳ ፣ ምንያህል ጥላሁን ገሠሠ ፣ውብሻው ስለሺ፣ መንበረ በየነ ፣ ትዕግስት ይልማ ፣ከበቡሽ ነጋሽ  ፣ ገነነ ኃይሌ፣ ጌታቸው ተካ ፣ ዓለማየሁ ግዛው… ፣ ሄለን በርሄ .ወዘተ ተጫውተዋል፡፡

አባቱ አቶ ማሞ በላይነህ ይባላሉ፡፡እናቱ ደግሞ ወ/ሮ ተድባበ ተሰማ፡፡ የተወለደው  በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሀገር ሰላሌ አውራጃ ሰላይሽ ጊዮርጊስ በተባለ ስፍራ ነው – ጥር 12  ቀን 1934 ዓ.ም፤ አየለ ትዳር የያዘው በ1962 ዓ፤ም ከወ/ሮ እልፍነሽ ወርቁ ጋር ነው፡፡ ሶስት ልጆችንም አፍርተዋል፡፡ትምህር የጀመረው በቤተክርስቲያን ውስጥ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ ከመጣም በኋላ ዲያቆን ሆኖ መርካቶ በሚገኘው ደብረ አሚን ተክል ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ቀድሷል፡፡

አየለ ከማንዶሊን ውጭ ሊድና ቤዝ ጊታር ይጫወታል፤ ድራምም ይሞካክራል፡፡ከሁሉም በላይ የውዝዋዜ አሰልጣኝ ስለነበር ለማሳየት መድረክ ላይ ወጥቶ ሲጨፍር ያስደንቃል፡፡ ለዚህም ነው ‹አየለ እኮ ውዝዋዜ ያደምቃል› የሚበላው፡፡

አየለ የግጥምና ዜማ አፍላቂ ነው፡፡ መጀመሪያ ግጥም ጽፎ ዜማ ማውጣት፤ አልያም ዜማ አውጥቶ ግጥም መፃፍ ለአየለ ቀላል ነው፡፡ ከሰራቸው ተወዳጅ ዜማዎች መሀከል አንዳንዶቹን መጥቀስ ለእማኝነት ያግዛልና እነሆ፡-

  • ለጥላሁን ገሠሠ ከሰራቸው መሀል የጣት ቀለበቴ ውሰጅ፤ ጠይም ናት ጠይም መልከ ቀና፤ ሁሉም በሀገር ነው፤በጥርሷ ሸኝታኝ አለችኝ ደህና እደር፤ናፍቆቷ ነው ያስጨነቀኝ፤ይገርማል ቁማናና ዛላ፤ወዘተ ለብዙነሽ በቀለ አምሮበታል ሙሽራው፤ለማህሙድ አህመድ ያባብላል አይኗ ያባብላል፤ ንገሯት መላ ትስጠኝ፤ለህብስት ጥሩነህ እንቡጥ ኝ፤ እናቴን አደራ፤

አየለ ወጣት ድምፃውያን ወደ አየለ መጥተው ዛሬም ‹ግጥምና ዜማ አለህ?› ቢሉት መልሱ ‹ሞልቶኛል› የሚል ነው፡፡አሁን አሁን አቅሙ ተዳከመ እንጂ በቀን  አንድ ግጥም ወይም ዜማ ሳይሰራ ውሎ አያድርም፡፡

-አንጋፋው ድምፃዊ፣ የዜማ እና የግጥም ደራሲ bአየለ ማሞ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ  መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ/ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

(ምንጭ፡- ቁም ነገር መፅሔት)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe