አደገኛ ዕፆችን በሰውነቷ ላይ ጠምጥማ በድብቅ ልታሳልፍ የሞከረች የውጭ ሀገር ዜጋ ተፈረደባት

ሉንጉ አኒንህ አንጎላዊት ነች፤ ጥር 19 ቀን 2014 ከብራዚል ሳኦፖሎ ከተማ በመነሳት የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመጠቀም ወደ አንጎላ ሉዋንዳ ከተማ ለመሄድ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለትራንዚት ባረፈችበት ወቅት በቦሌ ጉምሩክ ሰራተኞች አደንዛዥ እፅ ተገኝቶባታል ፤ግለሰቧ በተደረገላት ፍተሻ በሰውነቷ ላይ ማለትም በሁለቱ አግሮቿ ታፋ ላይ߹ በመቀመጫዋ አካባቢና በሆዷ ላይ በፕላስተር ጠቅልላ በማያያዝ 4 ( አራት ) እሽግ 4‚54 ( አራት ሺህ ስድስት መቶ አስራ አንድ ነጥብ ሃምሳ አራት ግራም ) የሚመዝን የኮኬይን ዕፅ መያዟ ይረጋገጣል፤

ተከሳሿ ልዩ ፍቃድ ሳይኖራት በህግ የተከለከሉ ዕፆችን ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር አስባ

የተገኘች በመሆኑ በፈፀመችው አደገኛ ዕፆችን ማዘዋወር የወንጀል ህግ አንቀፅ 525 (1)(ለ)ን በመተላለፏ ነው ክስ የተመሰረተባት ።

ክሱን የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ አስተርጓሚ ታግዛ የዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲደርሳት ተደርጎና ተነቦላት የእምነት ክህደት ቃሏን ስትጠየቅ ተከሳሽ ” በዐቃቤ ህግ የተመሰረተብኝን ክስ ተረድቼዋለሁ የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሚያለሁ የገንዘብ እጦት ስለነበረብኝና የ5 ልጆች እናት ስለሆንኩኝ ለልጆቼ ማሳደጊያ እና ለህክምና ብዬ ነው ወንጀሉን የፈፀምኩት በዚህም ጥፋተኛ ነኝ “ ስትል ቃሏን ሰጥታለች ።

ዐቃቤ ህግም ተከሳሽ አንደ ዐቃቤ ህግ የክስ አቀራረብ በድርጊቷ ተጸጽታ በዝርዝር ጥፋቷን ያመነች በመሆኑ ፍርድ ቤቱን የጥፋተኝነት ውሳኔ ይሰጥልኝ ሲል ጠይቋል ።

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ በማስተላለፍ በ5 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራትና በ5 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት አንድትቀጣ ወስኖባታል ።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe