የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም አዲስ ፓስፖርቶችን ይፋ አድርጓል።
ይህን ተከትሎ የበርካቶች ጥያቄ የሆነው የቀደሞ ፓስፖርታችንን በአዲሱ መቀየር አለብን ወይ? የሚለው ነው፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ነባሩ ፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜው እስኪያበቃ ጥቅም ላይ መዋሉን የሚቀጥል ሲሆን የዕድሳት ጊዜው ሲደርስ በአዲሱ ኢ-ፓስፖርት እንደሚተካ አሳውቋል፡፡
ማንኛውም ግለሰብ የአገልግሎት ዘመኑ ያላለፈበት ፓስፖርት ካለው መለወጥ ሳይጠበቅበት መጠቀም ይችላል፡፡
ይህ ማለት ግዜው ያላለፈ የቀድሞው ፓስፖርትና አዲሱ መሳ ለመሳ አገልግሎት እየሰጡ በመቆየት የቀድሞው የአገልግሎት ግዜው ሲጠናቀቅና ግለሰቡ እድሳት ሲያደርግ አዲሱን ኢ ፓስፖርት ማግኘት ይችላል ማለት ነው፡፡
አዲሱን ኢ-ፓስፖርት የሚጠይቅ ግለሰብ በሁለት ወር ከ10 ቀን ማግኘት የሚችል ሲሆን የአገልግሎት ዘመኑም ወደ 10 ዓመት ከፍ ተደርጓል፡፡

