አዲሱ የሒሣብ አያያዝና ሪፖርቲንግ ስርዓት ትግበራ ከፍተኛ መዘናጋት እየተስተዋለ ነው ተባለ

በምህፃረ ቃሉ IFRS ወይንም አለም አቀፉ የሂሳብ አያዝና ሪፖርቲንግ ደንብ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመላው አለም ሊባል በሚችል መልኩ ተግባራዊ እየሆነ ያለ ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝና ሪፖርት ማድረግያ ስርዓት ነው፡፡
ኢትዮጰያም ይህንኑ የሒሳብ አያያዝና ሪፖርት ማድረግያ ስርዓት ተቀብላ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረች አንድ አመት የሚሆን ጊዜ ተቆጥሯል፡፡
ኢትዮጵያ እስካለፈው አመት ድረስ የራሷ የሆነ የሒሳብ አያያዝ ወይም ሪፖርት ማደረግያ ደንብ እንደሌላት የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡
እንዲህ አይነቱ ስርዓት አለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን በእጅጉ ይጨምራል ነው የሚሉት፡፡
ምንም እንኳ አገሪቱ ካለፈው አመት ጀምሮ ይህንን የሒሳብ ስርዓት በይፋ ብትቀበልም አተገባበሩ ላይ ግን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች እንዳሉ ባለሙያ ይናገራል፡፡
አብዛኞቹም ከእውቀት ማነስ ጋር የሚያያዙ መሆናቸውን በመጥቀስ፡፡
የተወሰኑ ድርጅቶች ይህንን የሂሳብ ስዓት ተግባራዊ ቢያደርጉም በአብዘኞቹ ዘንድ ግን ከፍተኛ መዘናጋት ይስተዋላል የሚሉት ባለሙያው የኢትዮጵያ አካውንቲንግ እና ኦዲቲንግ ቦርድ ባወጣው ህግ መሰረት በዘንድሮው አመት ሁሉም ድርጅቶች የሂሳብ ሪፖርታቸውን በዚህ ስርዓት እንዲያቀርቡ እንደሚጠቀብ ጠቅሰው ሁሉም ድርጅት ከወዲሁ ይህንን ተግባራዊ ሊያደርጉ ይገባል ባይ ናቸው፡፡
SourceAhadu tv

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe