አዲሱ የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ አልበም – “ኢቶሪካ” በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ቻርት ላይ እየተደመጠ ነው

“ኢቶሪካ” የተሰኘው የቴዲ አልበም 18 ሙዚቃዎችን በውስጡ አካትቷል። አልበሙ በተለቀቀ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ “ጀንበር” የተሰኘው ዘፈኑ ከ31.5 ሚሊዮን በላይ እይታን ማግኘት ችሏል።

ቴዲ በሙዚቃዎቹ እንደተለመደው ኢትዮጵያዊነትን አቀንቅኗል፤ አንድነትን ከፍ የሚያደርግ ደማቅ መልዕክቱንም አስተላልፏል።

ቴዲ አፍሮ በአዲሱ አልበም፤ ከሌላው የሙዚቃ ሥራዎቹ በተለየ መልኩ በማንነታቸው ምክንያት በግፍ ለተገደሉ ዜጎች መታሰቢያ ያደረገ ሙዚቃ አቅርቧል።

ይህ “የአዞ እምባ” የተሰኘ መጠሪያ የሰጠው ሙዚቃው፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በማንነታቸው ብቻ ተለይተው በግፍ ለተገደሉ ንፁሃን ወገኖች እና ከቄያቸው ለተፈናቀሉ ፣ የአካልና የሥነልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን መታሰቢያነት ይሁንልኝ ብሏል።

“ዳስ ጣል (አንሳው)” በሚለው ሌላኛው ዘፈኑ ደግሞ:-

“በፍቅር ጠርተው ከዳር እስከዳር
መሃል ገቡና አቆሙን ከዳር”

ሲል የሀገሪቱን ፓለቲካ እና የፓለቲከኞች አካሔድ ታዝቧል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞቿ ዋጋ ከፍለው ለትውልድ ያሻገሯት መሆኗን በዚህኛው ዘፈኑ ገልጿል።

ይሁንና ይቺን ሀገር ተረክበን፣ በብሔር ተከፋፍለን ስለምን ኢትዮጵያዊነት ወደ ዳር እንገፋዋለን ? ሲል እንዲህ ይጠይቃል:-

“ባቆዩት ሀገር ጀግኖች በአንድነት በአርበኝነት
እንዴት ይገፋ ኢትዮጵያዊነት”

በተመሳሳይ መልኩ “ስምምነን” በተሰኘው የጉራጊኛ ሙዚቃው:-

“ተበትነን ብናይ ረብ የለን እንደብናኝ” ይለናል ቴዲ መከፋፈል ልክ እንደ ብናኝ የሚያሳንስ መሆኑን ለማመልከት።

“ይሆናል ወይ እቃ ድስት ያለክዳን”
እኛስ አለን እንዴ ሀገር ከሌለን”
እንዴት ስለለየን ፍረደ ገምድል ዳኛ
ዓባይ እየሞላ እንጎላለን እኛ” ብሏል ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe