የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ለተሸከርካሪ አስመጪዎች፤አዳዲስ ጥብቅ መስፈርቶችን በማውጣቱ ከኢንደስትሪው ተዋናዮች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ አስመጪዎቹ እንደሚሉት መስርቶቹ ተግባራዊ ሊሆኑ የማይችሉ ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ የአምራቾች ኃላፊነት የሆኑ መስፈርቶችን ከአስመጪዎች እንዲሟሉ መጠበቁ ንግዳቸውን አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል ካፒታል ዘግቧል፡፡
በአዲሱ መስፈርት ላይ ዋናው የአከራካሪ ጉዳይ ለተሸከርካሪዎች የተቀመጠው የባትሪ ደህንነት ማረጋገጫ ነው፡፡ ይህም አስመጪዎች የተሸከርካሪ ባትሪዎች ዓለም አቀፍ የደህንነት መስፈርቶችን እንዲያሟሉና እንዲያረጋግጡ ይጠይቃል፡፡
አስመጪዎቹ እንደሚሉት የባትሪ ደህንነት ማረገጋጫ ሊሰጥ የሚችለው አምራች እንጂ አስመጪ አይደለም በማለት ይከራከራሉ፡፡//

