አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የ”ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ” ውድድርን በደመቀ ሁኔታ አስተናገደች

ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር የቀጣይ ዓመት አስተናጋጅም አዲስ አበባ ናት
የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምልክት በሆነው በታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ፣ አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የ”ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ” ውድድርን በደመቀ ሁኔታ አስተናግዳለች።
በውድድሩ ላይ ከ35 ሀገራት የተውጣጡ 58 ምርጥ ተወዳዳሪዎች በኢትዮጵያ መድረክ ብቃታቸውን አሳይተዋል።
ተሳታፊ የውጭ ሀገር ዜጎች በአዲስ አበባ ንጽህና፣ አረንጓዴ ልማት እና ዘመናዊ መሠረተ ልማት መገረማቸውን ገልጸዋል።
“ገና አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረስኩ ነው መገረም የጀመርኩት” ያሉት ተወዳዳሪዎች፣ በኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባይነት መመሰጣቸውንም መስክረዋል።
ይህ ውድድር አዲስ አበባን በስፖርት ቱሪዝም የዓለም መዳረሻ ለማድረግ ትልቅ በር ከፍቷል።
የውድድሩ አዘጋጅ የሆነው ዓለም አቀፉ የብስክሌት ህብረት፣ ውድድሩ በሚቀጥለው ዓመትም በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰኑን በደስታ አብስሯል፡፡
ኢትዮጵያ በሩጫ ብቻ ሳይሆን፣ በብስክሌት ስፖርትም ነገ በዓለም መድረክ ደምቃ ለመታየት ዝግጁ መሆኗን በተግባር ያሳየችበት አጋጣሚ ሆኖ አልፏል።
(ታምራት ቢሻው – AMN)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe