አዲስ አበባ በኤች አይቪ ኤድስ በሽታ ስርጭት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፣ልደታ እና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ መሆኑ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ በኤች አይቪ ኤድስ በሽታ ስርጭት ከሌሎች ክልል ከተሞች ጋር ሲነፃፀር በሁለተኛ ደረጃ መቀመጡ ተገልጿል፡፡

በኤች አይቪ ኤድስ በሽታ በአዲስ መልክ የመያዝን ጉዳይ ከእናት ወደ ልጅ እንዲሁም ለስርጭቱ መንስኤ የሚሆኑ መሰል ተያያዥ ጉዳዮችን ለመቀነስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2025 እስከ 2030 ድረስ የበሽታውን መጠን እንዲቀንስ ለመድረግ እቅድ መያዙን የገለጹት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የኤች አይቪ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ዳይሬክተር ወ/ሮ ፈለቀች አንዳርጌ ናቸው፡፡

በአዲስ አበባ 1መቶ 26 ወረዳዎች መኖሩን ተከትሎ በ48 ወረዳዎች የበሽታው መዛመትና የሞት ቁጥሩ ከፍተኛ በመሆኑ በተለይም በአዲስ ክፍለ ከተማ ፣በልደታ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የስርጭቱ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ በአንደኝነት ተመዝግቧል ነው ያሉት፡፡
በበሽታው በዋናነት ተጠቂ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ተከትሎ ይህም የሚሆነው በአቻ ግፊት እና ኢኮኖሚን ለማስተካከል በወሲብ ንግድ የተሰማሩ በመሆኑ ብሎም እድሜያቸው እስከ 35 ድረስ ባሉት ሴቶች የሚስተዋል እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡

በኤች አይ ቪ ኤዲስ በሽታ ዙሪያ ጥናት የሚደረገው በዓመት አንድ ጊዜ በመሆኑ ቀደም ሲል በነበረው ዓመት ከ1ሺህ 4 መቶ ያላነሱ ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ መሆኑን ገልጸው በ2016 ዓ.ም የተደረገውን ጥናት ደግሞ ከታህሳስ 30 ጀምሮ የሚታወቅ ይሆናል ብለዋል፡፡

በኤች አይቪ ኤዲስ በሽታ ስርጭት ከሌሎች ክልል ከተሞች ጋር ሲነፃፀር በሁለተኛ ደረጃ መቀመጡን ገልጸው ነገር ግን ስርጭቱ ተባብሷል ማለት አይደለም ሲሉም ኃላፊዋ ያስረዳሉ፡፡ባለፉት 3 ወራት ብቻ በበሽታው ዙሪያ ከመተግበርና ከተጠያቂነት ጋር ተያይዞ ለችግሩ ምላሽ የመስጠት ክፍተት በቢሮው በኩል የታዩ ክፍተቶች መኖራቸውንም አልሸሸጉም፡፡

Via Ahadu

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe