አዲስ አበባ ከ3 ሺ በላይ ቤቶችን አፈረሰች፤ በርካታ ደንብ አስከባሪዎች መታሰራቸው ተሰማ፤

መንግስትና ህዝብ ሀገር የማዳን ዘመቻ ላይ መሆናቸውን ተገን በማድረግ በአዲስ አበባ በተላ ክፍተከተሞች የመሬት ወረራና ህግ ወጥ የቤቶች ግንባታ ተጧጥፈዋል፡፡

በመሆኑም ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታውን ከግምት ውስጥ በማስገባት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶችን የማፍረስ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት  ሲያስታውቅ በክፍለ ከተማው እስካሁን ከ3 ሺህ በላይ ቤቶች እና አጥሮች ላይ እርምጃ እንደተወሰደ ተገልጿል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ  እንደዘገበው የመሬት ወረራው የሚከናወነው በተለያዩ መንገዶች ነው፤ የመጀመሩያው የከተማው አሉ ተየተባኩ ስም ያላቸው ባለሀብቶች በትንሽ ገንዘብ ከአርሶ አደሮች ላይ መሬት መግዛት ቀዳሚው ሲሆን ራሱ አርሶ አደሩም መሬትን ተደራድሮ በመሸጥ ተመልሶ ሌላ ቦታ አጥሮ የመያዝ ሁኔታ ይስተዋላ ተብሏል፤

ከአሁን በፊት ቦታው ለልማት ተፈልጎ ካሳ የተከፈለባቸው መሬቶችም በወረራ ተይዘው በርካታ ቤቶች ተገንብተውበት መገኛታቸውን ነው ፅ/ ቤቱ ያመለከተው፡፡

የመንግስት ትኩረት ወደ ህልውና ዘመቻው መሆኑን በማጤን እጃቸውን ያስገቡ የክፍለ ከተማው አመራሮች ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ የሚናገሩት የፅ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ዘላላም ብርሃኑ እስካሁን ከ100 በላይ  የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቅሰዋል፤ የተወሰደው እርምጃ ምን እንደሆነ ባያብራሩም፤

ከፌደራል በፖሊስ ፤ ከደንብ ማስከበርና ከአጎራባች ሰበታ ከተማ አስተዳደር የተቀናጀ ግብረ ሃይክል በማቋቋም  አጥፊዎችን የማደን ስራ እየተሰራ መሆኑን አመልክተው የተወረሩ መሬቶችንም ወደ መሬት ባንክ እየገነባ መሆኑን ተናግረዋል፤

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በመላ አገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መተግበር ከጀመረ ወዲህ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ሕገወጥ የመሬት ወረራ መስፋፋቱን የከተማ አስተዳደሩ ያስታወቀ ሲሆን አገር ችግር ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም መሬት መውረር ከፍተኛ ወንጀል መሆኑን በመግለጽ፣ እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት ሕወሓትና ሸኔ ከሚፈጽሙት የሽብር ተግባር ተለይቶ እንደማይታይ መግለፁ ይታወሳል፤

SourceAMN

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe