አዲስ አበባ 88 ከፍተኛ አመራሮቿን ከስራ አባረረች፤

ምክንያቱ ከመሬት ወረራ ጋር የተያያዘ ሙስና ነው ተብላል፤ ዝርዝር አለን

በአዲስ አበባ ከተማ በህገወጥ መንገድ የተወረሩ 671 ቦታዎች ማግኘቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ጀማል አሊ ገልጸዋል፡፡

በመዲናዋ በህገወጥ መንገድ የተወረሩ 671 ቦታዎች የተገኙ ሲሆን

260ሺሕ 106 ካሬ ሜትር ይዞታዎች ወደ መሬት ባንክ መመለሳቸውንም ተናግረዋል፡፡

በህገወጥ የመሬት ወረራ ተግባር የተሳተፉ 88 በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደረጃ የነበሩ አመራሮች ከሥራ ገበታቸው ታግደው  አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛልም ተብሏል፡፡

በህገወጥ ወረራ የተያዙት ቦታዎች ካርታቸው ሙሉ በሙሉ መምከኑንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

መሬትን በህገወጥ መንገድ ለመውረር የሚደረገው ጥረት ከሽብር ቡድኑ አገር የማጥፋት ሴራ ያልተናነስ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ህገ ወጥ ወረራ በስፋት የተስተዋለባቸው ለሚ ኩራ፣ ቦሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe