አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለውይይት ሁኔታዎችን አመቻች እንጂ አደራዳሪም ሆነ እርቅ አስፈጻሚ አይደለም ተባለ፤

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮችና አባላትን ለምክክሩ የሚረዱ መድረኮችና አጀንዳዎችን በማመቻቸት አስፈላጊው ሥራ ለማከናወን የተመረጡ ግለሰቦች እንደሆኑ የገለፁት የሀገራዊ ምክር ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ  ኮሚሽኑ የድርድር ሥራ እንደማይሰራ፤ ዕርቅ እንደማያስፈጽም ሕዝብ ሊያውቅ ይገባል ብለዋል።

የኮሚሽኑ ዋና ሥራ አጀንዳ ነቅሶ ሕዝብን ለውይይት መጋበዝ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ለሕዝብ ከሚቀርቡት አጀንዳዎች ውስጥ መግባባት ላይ የሚያደርሰውን መንገድ እናመቻቻለን በዚህ አካሄድ ኮሚሽኑ አመቻች ሲሆን ዋናው ወሳኙ ሕዝብ ነው። ብለዋል

ምክክሩ ወደ ‘ ብሔራዊ እርቅ ‘ የሚወስድ ከሆነም በእራሱ አሰራርና አካሄድ መሰረት ወደ እርቅ ይሄዳል እንጂ ኮሚሽኑ ሽምግልና እና አሊያም ብሔራዊ እርቅ ማስፈጸም ውስጥ እንደማይገባ ፕፌሰር ምስፍን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ ኃላፊነት አካታች በሆነ መንገድ ሁሉንም ጉዳይ አለኝ የሚል ወገንን በተመረጡ አጀንዳዎች ላይ እንዲመክር ማድረግ ነው እንደሆነ ያብራሩት ኮሚሽነሩ አንዳንድ ጊዜ በተሳሳተ መንገድ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን አሸማጋይ አሊያም አደራዳሪ አድርጎ ማየት  የተሳሳተ ነው ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe