አፍሪካ የራሷ ችግር በራሷ መፍታት የምትችል አህጉር አይደለችም ሲሉ የአሜሪካ ከፍተኛ ዲፕሎማት ተናገሩ፤

በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የነበረው 10ኛው ጣና ፎረም ዛሬ ተጠናቋል። ፎረሙ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም የተዘጋጀ ሲሆን ለ3 ቀናት ሲካሄድ ነበር።

በዛሬ መርሃ ግብር ” የአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ስነ ምህዳር እና ምላሾች” በሚል ርዕስ ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዶ ነበር በውይይት አፍሪካዊያን ምሁራን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር አቴ ዌበር፣ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሀመር፣ የተመድ የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር ሀና ቴተህ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ተገኝተው ነበር።

በወቅቱም ኬኒያዊው የህግና ፖለቲካ ተንታኙ ፕ/ር ፓትሪክ ሉሙምባን ጨምሮ ሌሎች አፍሪካዊያን ምሁራን ለሐመር ጥያቄ አቅርበዋል።

ምሁራኑ ለአምባሳደር ሐመር ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ አፍሪካ የራሷን ችግር በራሷ እንድትፈታ ለምን አትተዋትም? የሚል ሲሆን አሜሪካ በአፍሪካ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እየገባች ነው፤ ቻይና ለአፍሪካ ከአሜሪካ በተሻለ መንገድ እየሰራች ነው የሚሉና ሌሎች ጉዳዮችን አንስተዋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር ፦ ” አፍሪካ በራሷ ችግሯን መፍታት ትችላለች ወይ ?  ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ  እንደዛ ማድረግ የምትችል አይመስለኝም። ሲሉ መልሰዋል፤

እኔ ባህርዳር የተገኘሁት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ለመንገር አይደለም።  ያሉት ሐመር አፍሪካም ሆነች አሜሪካ ችግራቸውን ለመፍታት በጋራ መስራት ግን አለባቸው። ብለዋል፤

በአፍሪካ እንደ አሜሪካ ብዙ ገንዘብ ኢንቨስት ያደረገ ሀገር ወይም ተቋም የለም፣ የአፍሪካዊያንን ህይወት በመታደግ ከአሜሪካ በላይ የሰራ ሀገር የለም፣ ፍጹም ላንሆን እንችላለን።ያሉት ማይክ ሐመር

አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለባትን ሀላፊነት ታውቃለች ነገር ግን በብዙ መንገድ ለአፍሪካ ድጋፍ እያደረግን እንገኛለን። ” ሲሉ መልሰዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe