ኡጋንዳና ግብፅ “በወታደራዊው መረጃ” ልውውጥ መስክ ለመተባበር ተስማሙ

አዲስ አበባ ከአቋማ “ዝንፍ” ባትልም ሰሞኑን ከወደ ካይሮ የዛቻ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው፡፡

ሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ስምምነት ያደረጉት በግብፅ እና ኢትዮጵያ መካከል “ውጥረት” በነገሰበት ወቅት ነው

ኡጋንዳ በወታደራዊ መረጃ ልውውጥ ዘርፍ ከግብፅ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችላትን ስምምነት መፈራረሟን ትናንት ረቡዕ መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አስታውቃለች፡፡ ስምምነቱ በሕዳሴ ግድብ ምክንያት በግብፅ እና ኢትዮጵያ መካከል “ውጥረት” በነገሰብት ወቅት የተደረገ መሆኑ፣ ጉዳዮን አነጋጋሪ አድረጎታል፡፡

ሰምምነቱን የተፈራረሙት በኡጋንዳ መከላከያ ኃይል የውትድርና መረጃ ኃላፊ እና የግብፅ መረጃ ዲፓርትመንት ተወካይ ናቸው፡፡

የካይሮን ልዑካን ቡድንን በመምራት ወደ ካምፓላ ያቀኑት የግብፅ ወታደራዊ መረጃ ሹም ሜ/ጀነራል ሳሜህ ሳበር በስምምነቱ ወቅት “ኡጋንዳ እና ግብፅ የናይልን ውሃ የደሚጋሩ እንደመሆናቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ትብብር መኖሩ የግድ ነው፡፡ ምክንያቱም የአንዱ ፍላጎት በቀጥታም ሆነ በሌላ መንገድ ሌላኛው ላይ ተፅእኖ መፍጠሩ አይቀርምና” ማለተቻው ተገልጿል፡፡

የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ የግብጽ የውሃ ድርሻ ከቀነሰ “ምስራቅ አፍሪካ ለከፍተኛ ቀውስ ይዳረጋል” ካሉ ከሳምንት ያክል ቆይታ በኋላ ፣ የሕዳሴው ፕሮጀክት የግብፅን የውሃ መጠን የሚቀንስ ከሆነ “ውጤቱ ከባድ ይሆናል”ሲሉ በትናንትናው ዕለት በድጋሚ ዝተዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ በድጋሚ ዛቻ አዘል ንግግር ያደረጉት በኪንሻሳ የተካሄደው የኢትዮጵያ ፣ የግብፅ እና የሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ያለውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው፡፡

ኡጋንዳ ቀድም ሲል ግብፅ በላይኛቹ የተፋሰስ ሀገራት የሚከናወኑ ፕሮጅክቶችን ለመቆጣጠር የምትሄደውን “ያልተገባ ርቀትና ሙከራ” ስትቃወም እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

አሁን ላይ ሁለቱ ሀገራት “በወታደራዊ መረጃ” ልውውጥ መስክ አብረው ለመስራት የመስማማታቸው ዓላማ ምን እንደሆነ ግን በሮይተርስ ዘገባ ላይ የተገለጸ ነገር የለም፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe