ኡጋንዳ “የሞቱ ምዕራባውያን” ልብስ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እግድ ጣለች!

የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዮሪ ሙሰቨኒ የሀገር ውስጥ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎችን እድገት ያቀጭጫሉ ያሏቸውን “የሞቱ ምዕራባውያን” ልብሶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ እገዳ ጥለዋል።ኡጋንዳ ከፍተኛ መጠን ያለው ያገለገለ ልብስ ስታስገባ የቆየች ሲሆን የዋጋ ቅናሽ ስላላቸው በተወሰኑ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተመራጭ ናቸው።

ነገርግን የሀገር ውስጥ የጨርቃጨርቅ ድርጅቶች ያገለገሉ ልብሶች ገበያው ላይ መብዛት የሀገሪቱን የጥጥ እና የጨርቃጨርቅ እንዱስትሪ እድገት ይገታዋል የሚል ቅሬታ እያቀረቡ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።ፕሬዝደንት ሙሰቨኒ”እነዚህ ለሞቱ ሰዎች የሚሆኑ ናቸው። ነጭ ሰው በሚሞትበት ጊዜ፣ ልብሶቹን ይሰበስቡና ወደ አፍሪካ ይልኳቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

የእንግሊዙ ግበረሰናይ ድርጅት ኦክስፋም እንደገለጸው ከሆነ የእርዳታ ድርጅቶች ከሜሪካ እና አውሮፖ ከሚሰበስቡት 70 በመቶ የሚሆነው ልብስ ወደ አፍሪካ ይላካል።ሮይተርስ ከሞቱ ሰዎች የሚመጣው ልብስ ምን ያህል ድርሻ እንዳለው ማረጋገጥ እንደማይችል ገልጿል።”አዲስ ምርት የሚያመርቱ ሰዎች እዚህ አሉን ነገረግን ገበያውን ሰብረው መግባት አልቻሉም” ብለዋል ሙሰቨኒ።

ኡጋንዳ ከፍተኛ የጥጥ አምራች ሀገር ብትሆንም አብዛኛው ምርት በተወሰኑ ደረጃ እሴት ተጨምሮበት ወደ ውጭ የሚላክ ነው። ኡጋንዳ አባል የሆነችበት የምስራቅ አፍሪካ ቡድን ያገለገሉ ልብሶች እንዳይገቡ በፈረንጆቹ 2016 ተስማምተው ነበር። ነገርግን አስካሁን ተግባራዊ ያደረገችው ሩዋንዳ ነች።

Via Al ain

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe