​ኢራን ለደረሰው ጥፋት ካሳ እንድትከፍል የአረብ ሊግ በጋራ ጠየቀ

​የአረብ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ፣ ኢራን በሀገራቱ ላይ ላደረሰችው ጥቃት እና ለሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት ተጠያቂ እንድትሆንና ተመጣጣኝ የካሳ ክፍያ እንድትፈጽም በጋራ ጠየቁ።
​በባህሬን ሰብሳቢነት በቪዲዮ ኮንፈረንስ የተካሄደው የአረብ ሀገራት ስብሰባ
​ ኢራን በጆርዳን፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ በባህሬን፣ በሳውዲ አረቢያ፣ በኦማን፣ በኳታር፣ በኩዌት እና በኢራቅ ላይ ለፈጸመቻቸው ጥቃቶች “ሙሉ ዓለም አቀፍ ተጠያቂነት” እንዳለባት ታውጇል።
​ በሀገራቱ ላይ ለደረሰው ጥፋትና ኪሳራ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ኢራን ሙሉ ካሳ የመክፈል ግዴታ እንዳለባት ሚኒስትሮቹ በአጽንኦት ገልጸዋል።
​ ከዚህ ቀደም ኢራን በተመሳሳይ መልኩ ሳውዲ አረቢያንና ሌሎች ጎረቤት ሀገራትን “በእኔ ላይ ለተከፈተው ጦርነት ተባባሪ ናቸው” በማለት ካሳ ጠይቃ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ የአረብ ሀገራቱ አሁን የወሰዱት አቋም ለዚህ ምላሽ የሚሰጥ ይመስላል።
​የስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ ሰርጥ የባህር ላይ ጉዞ ደህንነትን ለማስጠበቅና ቀጠናዊ መረጋጋትን ለመፍጠር አዳዲስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ተጀምረዋል፦
​ በእንግሊዝና በፈረንሳይ የሚመራ ዓለም አቀፍ ወታደራዊ ውይይት በለንደን እየተካሄደ ይገኛል።
​በአካባቢው ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና የዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ የዓለምን የነዳጅ ዋጋ እና የንግድ መስመር በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈታተነው ይገኛል።
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በፈጸመው ጥቃት ሦስት የጭነት መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ መመታታቸውን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።
አብዮታዊ ዘቡ እርምጃ ከወሰደባቸው ሦስት የጭነት መርከቦች መካከል ሁለቱን እንደያዘ አስታውቋል።
በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያለው የመርከቦች እንቅስቃሴ በኢራን እና በአሜሪካ ኃይሎች ማስጠንቀቂያ ውስጥ ባለበት ጊዜ ኢራን መመሪያዋን አልተከተሉም ባለቻቸው መርከቦች ላይ እርምጃ እየወሰደች ነው።
የዩናይትድ ኪንግደም የባሕር ትራንስፖርት ንግድ ማዕከል እንዳሳወቀው የአብዮታዊ ዘቡ “አጥቂ ጀልባ” በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ሲጓዝ በነበረ የግሪክ ኩባንያ ንብረት በሆነ ኮንቴይነሮችን በጫነት መርከብ ላይ ተኩስ ከፍቶ ከባድ ጉዳት አድርሷል።
በተጨማሪም የተለያዩ ምንጮች እንዳረጋገጡት ንብረትነቱ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የሆነ እና የፓናማን ሰንደቅ ዓላማ በሚያውለበልብ መርከብ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። በመርከቡ እና በሠራተኞቹ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰም ተብሏል።
የባሕር ትራንስፖርት ደኅንነት ተቋም የሆነው ቫንጋርድ ለቢቢሲ እንዳሳወቀው ሌላ የፓናማን ሰንደቅ ዓላማ የሚያለውበልብ መርከብ ከሆርሙዝ ወሽመት በሚወጣበት ጊዜ የጥቃት ዒላማ ሆኗል። በጥቃቱም በመርከቡ የተለያዩ ክፍሎች ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ተዘግቧል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጥቃት ከተፈጸመባቸው ሦስት መርከቦች ሁለቱ “ፈቃድ ሳያገኙ እና የመርከብ እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ ሥርዓታቸውን በማጥፋታቸው” በቁጥጥር ስር ውለው ወደ ኢራን የባሕር ዳርቻ መወሰዳቸውን አስተውቋል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe