ፕሬዝዳንት ፔዜሽኪያን ሁኔታው ለመላው ኢራናዊያንን ትልቅ ድል ነው በማለት ገልጸውታል፡፡ መረጃው የወጣው ኢራን በኩዌት እና ባህሬን ላይ ጥቃት ካደረሰችና ውጥረቶችም ከተባባሱ በኋላ ነው፡፡ ኢራን ትላትን እሁድ ከአሜሪካ ለደረሳበት ጥቃት በቀል በባህሬንና ኩዌት ላይ የሚሳኤል ጥቃት ፈጽማለች፡፡
ይህ የሆነውም ኢራንና ኳታር በደረሱት ስምምነት እንደሆነ ታስ አስነብቧል፡፡ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ቀሪ የተያዘውን ሃብትም ለማስለቀቅ ስራዎች ቀጥለዋል ብለዋል፡፡ ምንም እንኳን ፕሬዝዳንቱ መልካም ያሉትን ዜና ለህዝባቸው ቢያሰሙም፤ከአሜሪካ ባለስልጣናት በኩል ግን ሁኔታውን የሚያረጋግጥ ምንም አይነት መረጃ አልወጣም፡፡ በተመሳሳይ በኳታር በኩልም እስካሁን የተሰጠ ማረጋገጫ አልተሰማም፡፡
ቴህራን ይህን ዜና ያሰማችው ከ ዋሽንግተን ጋር ያለው ድርድር በብዙ እየተፈተነ ባለበት በዚህ ስዓት ነው፡፡
ፓኪስታን ዋሽንግተን እና ቴህራን ከሰሞንኛው መጠቃቃት በኋላ ዳግመኛ ቴክኒካዊ ንግግር ነገ ማክሰኞ እንደሚጀምሩ ይፋ አድርጋለች፡፡ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደርም ፓኪስታን ያለችው ቴክኒካዊ ንግግር በመጪዎቹ ቀናት ይደረጋል ብሏል፡፡//

