ኢራን በ12ቱ ቀናት ጦርነት ከኒውክሌር ሳይንስ ጋር የተገናኘ እውቀት ያላቸው 14 ሳይንቲስቶቿ በእስራኤል ተገድለውባታል ተባለ

ኢራን በ12ቱ ቀናት ጦርነት በህይወት የተረፉ የኒውክሌር ሳይንቲስቶቿን ወደ ጥብቅ ቦታ በመውሰድ ይዛቸዋለች ተባለ፡፡ በሰኔው የ12ቱ ቀናት ጦርነት ከኒውክሌር ሳይንስ ጋር የተገናኘ እውቀት ያላቸው 14 ሳይንቲስቶቿ በእስራኤል ተገድለውባታል፡፡ ከ15 በላይ ከፍተኛ የኒውክሌር ሳይንቲስቶቿን ከመኖሪያበቤታቸውና ከሚያስተምሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በማስወጣት ደህንነቱ የተረጋገጠ ነው ወደተባለ ስፍራ ወስዳቸዋለች ተብሏል፡፡

ኢራን በእስራኤል ከ14 በላይ ጥናትና ምርምር የሚያደርጉ ሙህራኖቿን ካጣች በኋላ አሁን በህይወት ያሉትን ሳይንቲስቶች በጥብቅ ሁኔታ እየጠበቀች ነው ተብሏል፡፡ አብዛኛዎቹ ሳይንቲስቶች ከግል መኖሪያ ቤታቸው እንዲወጡ ተደርገው መንግስት ባዘጋጀላቸው ጥብቅ ቦታ መኖር ጀምረዋል ሲል ቴሌግራፈ ዘግቧል፡፡እንደዘገባው ከሆነ 15 ሳይንቲስቶች በእስራኤል ስማቸው ተመዝግቦ ከሚገኙ 100 ኢራናዊያን ሳይንቲስቶች መካከል ይገኙበታል፡፡

እነዚሁ በዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩ ሳይንቲስቶች ሌሎች ከኒውክሌር ፕሮግራም ጋር የተያያዘ ግንኙነት በሌላቸው መምህራኖች እንዲተኩ እንደደረገም ተሰምቷል፡፡ በ12 ቀናት ጦርነት ወቅት ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መገደላቸው ይታወሳል፡፡ ባለፈው ሳምንት ኢራን በራሷ እጅ ሩዝቤይህ የተሰኘውን የኒውክሌር ሳይንቲስቷን ከሞሳድ ጋር ግንኙነት አለው በሚል በስቅላት መግደሏም ይታወሳል፡፡ ሩዝቤይህ ባልደረባው የሆነውን ሳይንቲስት እንዲገደል በ12ቱ ቀናት ጦርነት ወቅት መረጃ ሰጥቷል በሚል ነበር በሞት እንዲቀጣ የተወሰነበት፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን ፖሊስ በ12ቱ ቀናት ጦርነት 21ሺ ተጠርጣሪዎችን መያዙን ገልጻል፡፡ ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል ከ260 በላይ የሚሆኑት በስለላ ወንጀል የተጠረጠሩ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ 172 የሚሆኑት ደግሞ ያልተፈቀዱ ቪዲዮዎችን በመቀርጽ የተያዙ እንደሆኑ ተናግሯል፡፡ ኢራን ባለፈው ወር ብቻ ሰባት ለእስራኤል በመሰለል የተጠረጠሩ ወንጀለኞችን በሞት ቀጥታለች፡፡ በሰኔው ጦርነት ኢራን ከፍተኛ ወታደራዊ ኮማንደሮችን፤ሳይንቲስቶችን ጨምሮ 1ሺ100 ዜጎቿን አጥታለች፡፡ በእስራኤል ላይ ባደረሰቸው የሚሳኤል ጥቃት ደግሞ 28 እስራኤላዊያንን መግደሏ ይታወቃል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe