ኢራን ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር ስትነጻጸር የጥንካሬዋ ምንጭ ተዋጊ ጄቶች ሳይሆኑ ሚሳኤሎቿ ናቸው ተባለ

ኢራን ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር ስትነጻጸር የጥንካሬዋ ምንጭ ተዋጊ ጄቶች ሳይሆኑ ሚሳኤሎቿ ናቸው ጥንካሬን የሚያላብሳት፡፡

ኢራን ታጥቃ የምትገኘው የውጊያ ተዋጊ አውሮፕላን ከ40 እና ከ50 ዓመት በፊት የተገዙ ናቸው ተባለ፡፡ እነርሱም ከአሜሪካ ጋር ሰላም በነበረችበት የተገዙ ስለመሆናቸው ይነገራል፡፡

ኢራን ከአዘርባጃን እስከ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ዘመናዊ የአየር ስርዓት ባላቸው ሀገራት ተከባ ትገኛለች፡፡

ይህም ለቴህራን በቀጠናው በሚነሱ ግጭቶች የእስትራቴጂክ ጠቀሜታን እንድታጣ ያደርጋታል እየተባለ ነው፡፡

አዘርባጃን ቱርክ ሰራሽ የሆኑ ባይራክተር ቲቢ2 የተሰኙ እና የእስራኤል ምርት የሆኑ ድሮኖችን ስለመታጠቋ ይነገራል፡፡ በተጨማሪም ከቱርክ ጋር ወታደራዊ ትብብር የምታደርግ ሲሆን፤በተዘዋዋሪ በኔቶ እስታንዳርድ የሚስተካከል ስልጠና እና ቴክኖሎጂ እንደምታገኝም ይገለጻል፡፡

ቱርክ  በቀጠናው የአየር ሃይላቸው ጠንካራ ናቸው ተብለው ከሚጠቀሱ ሀገራት በፊት መስመር የምትገኝ ናት፡፡ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ፡ኳታር እና ሳውዲ ዘመናዊ የሚባሉ የአየር ሃይል አቅም ያላቸው እንደሆኑ ይነገራል፡፡

በአንጻሩ ኢራን የአየር ሃይሏ ከሌሎቹ አንጻር እጅግ ደካማ እንደሆነ ነው የሚገለጸው፡፡ በቀደመው ጊዜ ከአሜሪካ የገዛቻቸው ጄቶች ማለትም ኤፍ 4 ኤፍ 5 እና ኤፍ 14 እንዳላት ይነገራል፡፡

በርግጥ ወታደራዊ ጄቶችን ከቻይና እንዲሁም ከሩሲያ የምትገዛ ቢሆንም በቁጥር እጅግ ዝቅተኛ መሆናቸውን ነው ዘገባዎች

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe