በሐረሪ ክልል ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ በብድር መልክ የተከፋፈለው ገንዝብ በአግባቡ እየተመለሰ አለመሆኑ ተገልጿል። የክልሉ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ በተዘዋዋሪ ፈንድ በ2011 ዓ/ም ከውዝፍ ለመሰብሰብ ካቀደው 9 ሚሊዮን ብር ማስመለስ የቻለው 440 ሺህ ብር ብቻ ነው። በዚሁ በ2011 ዓ/ም በብድር እና ቁጠባ ተቋም በኩል ተከፋፍሎ መመለስ ከነበረበት 84 ሚሊዮን ብር የተመልሰው ከ 1 በመቶ አይበልጥም።
<የቆሰሉት የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እየታከሙ ነው>
ኢንተርፕራይዙ ብድር ማስመለስ ባለመቻሉ ሌሎች ተጠቃሚ መሆን የሚገባቸው ወጣቶች ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻሉ ተገልጿል። በሌላ በኩል በሐረሪ ክልል ከ62 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው የተገነቡ የማምረቻ እና የመሸጫ ሼዶች በአግባቡ ጥቅም ላይ እየዋሉ አይደለም። በዚህም የህዝብ እና የመንግስት ሃብት እንዲባክን ሆኗል።
እነዚህ የማምረቻ እና የመሸጫ ሼዶች በኪራይ መልክ አገልግሎት ቢሰጡ በየዓመቱ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ የሚያስገቡ መሆኑን የሀረሪ ክልል ዋና ኦዲተር ቢሮ ጥናት አመላክቷል። * የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ ስራ አጥ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ ከ2009 ጀምሮ በመንግስት በጀት መተግበር የጀመረ ፕሮጀክት ነው።
መረጃ ምንጭ ፦ ከ’ብርቱ ወግ/የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን’ ፕሮግራም