“ኢቢሲ ስፒከር አይደለም ” ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

” ኢቢሲ የመንግሥት አፍ ያልሆነ መሆን አለበት ” – ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ብሔራዊ የቴሌቪዥን እና ሬድዮ ጣቢያ የሆነው ኢቢሲ ” የመንግሥት አፋ ያልሆነ ፤ ለሚያራግቡ እና ለማያስጮሁ ሰዎችም መሳሪያ ያልሆነ መሆን አለበት ” ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ የኢቢሲ የሚዲያ ኮምፕሌክስን መርቀው ሲከፍቱ ነው።

በዚህ ስነስርአት ላይ ንግግር ያደረጉት ጠ/ሚኒስትሩ ፤ ” ኢቢሲ ለመንግሥት ብቻ የሚያገለግል ሳይሆን ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርግ ሚዲያ እንደምታድረጉት ተስፋ ይደረጋል ” ብለዋል።

” ኢቢሲ ስፒከር አይደለም ” ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ” የሚነገርን ድምፅን የሚያጎላ ሳይሆን ድምፅ የሚፈጥር መሆን አለበት ፤ በየቦታው ለማስጮህ ፌስቡክ አለ በቂ ነው ፤ ማስጮህ ሳይሆን የሚጮኸውን ነገር መፍጠር ነው የሚያስፈልገው ” ሲሉ ተደምጠዋል።

” መንግሥት ሲያበላሽ ቆንጠጥ አድርጎ የሚጠይቅ ፤ የመንግስት አፍ ያልሆነ ፤ ለሚያራግቡ እና ለሚያስጮሁ ሰዎች መሳሪያ ያልሆነ ፤ የኢትዮጵያን ልዕልና ከፍ የሚያደርግ ፤ የኢትዮጵያን ፍላጎት ከፍ የሚያደርግ ተቋም መሆን አለበት ” ብለዋል።

” ኢቢሲ ከሰፈር ጨዋታ ወጥቶ በአፍሪካ ደረጃ የኢትዮጵያን ታሪክ ፤ የኢትዮጵያን ተፈጥሮ ሃብት ፤ ሊጎበኙ የሚገባቸውን ቦታዎች፣ ያሉትን የስራ እድሎች መግለጥ ይጠበቅበታል ” ሲሉ አክለዋል።

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመረቁት ሸጎሌ አካባቢ የሚገኘው የሚዲያ ኮንፕሌክስ እጅግ በጣም ዘመን አፈራሽ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ያሉት፣ ውስጣዊውም ሆነ ውጫዊ ገፅታ ለስራ እጅግ በጣም ምቹ የሆነ ነው።

ብሔራዊው የቴሌቪዥን እና ሬድዮ ጣቢያ ኢቢሲ የመንግሥት እና የአንድ ፓርቲ ልሳን በመሆን እና የብዙሃንን ድምፅ ያፍናል በሚል የሚተቹት በርካቶች ናቸው።

የ ” ኢህአዴግ ” ለውጥ ተደርገ በታባለባቸው ጥቂት ወራት ውስጥ ጣቢያው በበርካቶች ዘንድ በሚዲያው ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ለውጥ እንደታየበት ሲገለፅ የቆየ ሲሆን በኃላ ላይ ግን የ ” መንግሥት ” እንዲሁም የአንድ የገዢ ፓርቲ ድምፅ በመሆንና ” ድምፃችን ሊሰማ ይገባል ” የሚሉ አካላትን ድምፅ ባለማስተላለፍ እንዲሁም የሚተላለፉ መልዕክቶችን በራሱ መንገድ ቀይሮ በማስተላለፍም ይወቀሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe