ኢትዮጵያዊው ኤርሚያስ አየለ የሮም ማራቶን ሩጫን በባዶ እግሩ በመሮጥ በስኬት አጠናቀቀ

የቀድሞ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሥራ እስኪያጅ ኤርሚያስ አየለ የሮም ማራቶን የሩጫ ውድድርን ሙሉውን በባዶ እግሩ ሮጦ በማጠናቀቅ አትሌት አበበ ቢቂላን ዘክሮታል።

አትሌት አበበ ቢቂላ ከ63 ዓመታት በፊት ሮም ላይ በባዶ እግሩ ሮጦ ለአፍሪካ የመጀመሪያውን የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ በማራቶን ማስገኘቱ ይታወሳል።

በጊዜው ውድድሩን 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዝግቦም ነበር።

ባለፉት ሁለት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የጓዳና ላይ ሩጫዎች እንዲሁም በሐዋሳ ግማሽ ማራቶን ላይ በባዶ እግሩ የሮጠው ኤርምያስ አየለ ማራቶንን በባዶ እግሩ ሲሮጥ የሮም ማራቶን የመጀመሪያው ነው።

ኤርሚያስ በቀጣይ ዓመት የግሪክ ማራቶን፣ የቶኪዮ ማራቶን እና በፈረንሳይ በሚካሄደው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ በልዩ ጥያቄ ላይ በባዶ እግሩ ለመሮጥ ዕቅድ አለው።

©EBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe