ኢትዮጵያዊው የ25 ዓመት ወጣት በአሜሪካ የ100 ዓመት የእስር ቅጣት ተበየነበት

በአሜሪካን ሃገር በስራ ባልደረባው ግድያ ክስ የተመሰረተበት ኢትዮጵያዊው የ25 ዓመት ወጣት ባዘን በርሄ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት የፌርፋክስ ካውንቲ ዳኛ የ100 ዓመት የእስር ቅጣት ተበየነበት።
በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና የአሜሪካ ፖሊስ እንደሚሉት ባዘን በርሄ የተባለው ግለሰብ፤ ከ1 ዓመት በፊት በአሜሪካን ሃገር ኤፕሪል 14 ቀን 2021 ዓ /ም በሚሰራበት በቨርጂኒያ ግዛት የታርጌት መደብር ውስጥ ከስራ ባልደረባው ጋር ይጣላል፣ የፀባቸው መንስዔ ደግሞ የዕዳት ሰራተኛ የሆነው የ58 ዓመቱ ሄርናን ሊቫ የተባለ ግለሰብ በማቀዝቀዥ ፍሪጅ ውስጥ አስቀምጨው የነበረውን ምሳዬን እኔ ሳላውቅ ምግቤን ሰርቆ በልቷል የሚል ነበር፡፡
የ24 ዓመቱ ባዘን በበነጋታው መዶሻና ቢላዎችን በመግዛት የግድያ ልምምድ ሲያደርግ እንደቆየ ፖሊስ አሳውቋል፣ በሚቀጥለው ቀንም ኤፕሪል 17 ቀን 2021 ዓ /ም የመስሪያ ቤታቸው የመኪና ማቆሚያ ላይ ተጠቂውን አድፍጦ በመጠበቅ በቢላዋ ደጋግሞ በመውጋትና በመዶሻ በመቀጥቀጥ ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል ሲል የፖሊስ ሪፖርት ያስረዳል ፡፡
የአሜሪካ ፖሊስ እንደሚለው ከሆነ መረጃዎች ወደ ተጠርጣሪው ከመጠቆማቸው በፊት ወዲያው እጁን ለፖሊስ የሰጠ ሲሆን በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ፍርዱን እየተጠባበቀ ነበር፡፡
የአሌክሳንድሪያ ነዋሪ የነበረው ባዘን ወንጀሉን እንደፈጸመ ያመነ ሲሆን ለተጠረጠረበት የግድያ እና ያለ አግባብ የሰውን ልጅ በጭካኔ መሳሪያ በመጠቀም መግደል በሚሉ ወንጀሎች፤ የፌርፋክስ ካውንቲ ጁሪ ባሳለፍነው ዓመት መጨረሻ በወርሃ ኦክቶበር አካባቢ ጥፋተኛ እንደሆነ ብይን ሰጥቶበት ነበር። ትላንት ጃንዋሪ 30 ቀን 2024 ዓ /ም ለመጨረሻ ውሳኔ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ዳኛው ለ100 ዓመት ወህኒ እንዲወርድ ፈርደውበታል፡፡
ዳኛው ለ25 ዓመት ወጣቱ ባዘን በርሄ ትላንት የ100 ዓመት የእስር ቅጣት ብይን ከመስጠታቸው በፊት ታዲያ፣ ባዘን ዳኛውን ድምጹን ከፍ አርጎ ደጋግሞ ከባድ ቅጣት እንዲጥሉበት የሟች ቤተሰቦች በተገኙበት መካከል ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን፣ ከባድ የእስር ቅጣት የማይበየንበት ከሆነ ግን ሌሎች ሰዎችን በተጨማሪ ሊገድልና ሊጎዳ እንደሚችል በዛቻ ባልተለመደ ሁኔታ ፍርድ ቤቱን ያስፈራራ እንደነበር በፍርድ ቤቱ የታደሙ የwusa9 ጋዜጠኞች ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe