ኢትዮጵያ ለዲፕሎማቶች እና ለአለም አቀፍ ሰራተኞች የለይቶ ማቆያ ግዴታዎችን አስቀረች

ኢትዮጵያ ከውጪ አገር የሚመለስ ማንኛውም መንገደኛ ለለይቶ ማቆያ በተመረጡ ሆቴሎች ለ 14 ቀን ተለይቶ እንዲቆይ ያስቀመጠችውን ግዴታ ለዲፕሎማቶች እንዲሁም በሀገሪቱ ለተመዘገቡ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ሰራተኞች አላላች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተቋማቱ በላከው ደብዳቤ ከማክሰኞ ግንቦት 18፤ 2012 ጀምሮ የሚመለሱ ዲፕሎማቶች እና የየድርጅቶቹ ሰራተኞች በመኖሪያ ቤታቸው ወይም በየኤምባሲዎቻቸው ውስጥ ተለይተው መቆየት እንደሚችሉ ገልጿል።

Read also:በጤና ተቋማት የሳይበር ጥቃቶች መጨመራቸዉ ተሰማ

ውሳኔው የሚመለከታቸው በአለም አቀፍ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ የዲፕሎማቲክ እና የሰርቪስ ፓስፖርት ያላቸው ሰዎች እንዲሁም የቅርብ ቤተሰቦቻቸው እንደሆነም ይፋ ተደርጓል። የተጠቀሱት ግለሰቦች “ከዚህ በኋላ መንግስት በለያቸው ሆቴሎች ራሳቸውን እንዲያገልሉ አይጠበቅባቸውም። ነገር ግን የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ለ14 ቀን ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ ይጠበቅባቸዋል” ሲል ሚኒስቴሩ በደብዳቤው አመልክቷል።

Read also:የጤፍ የባለቤትነት ጥያቄ ክስ በገንዘብ እጥረት ሳቢያ መመስረት አልተቻለም ተባለ

ግለሰቦቹ ወደ አገር ውስጥ ከመመለሳቸው በፊት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ራሳቸውን ለይተው የሚቆዩበትን አድራሻ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሚኒስቴሩም ለሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ክፍሎች ያስታውቃል። ማንኛውም ተመላሽ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሊከናወኑ የሚገባቸው ተግባራትን በተመለከተ የወጡ መመሪያዎችን የመተግበር ግዴታዎች እንዳሉበት ሚኒስቴሩ ገልጿል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe