በቢሾፍቱ እየተካሄደ ባለው የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሚኒኬሽን ጉባኤ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ.ር) ሲናገሩ እንደሰማነው ኢትዮጵያ ለጅቡቲ በቀን 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ የመጠጥ ውሃን እያቀረበች ነው
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገር ጋር ባላት የመሰረተ ልማት ትስስር ለበርካታ ዓመታት ንፁህ የመጠጥ ውሃን ለጅቡቲ ስታቀርብ እንደነበር አንስተው በአሁኑ ሰዓት በቀን የሚቀርበው የውሃ መጠን 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ደርሷል ብለዋል።
#የንፁህ_መጠጥ_ውሃ ፕሮጀክቱ በሁለቱ ሀገራት የውሃ ስምምነት መሰረት ከስምንት ዓመት ገደማ በፊት ከቻይና መንግስት በተገኘ ብድር ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ነው።
የከርሰ ምድር ጉድጓዶችን በሶማሌ ክልል ሺንሌ በመቆፈር የመጠጥ ውሃው በሚሎ፣ሐረዋ፣አዲጋላ፣ለአስራት፣አይሻ፣ደወሌ አድርጎ 258 ኪሎ ሜትር ተጉዞ ጅቡቲ ይደርሳል።
ፕሮጀክቱ ከዚህ ቀደም ሲጀመር ውሃ ለመሳብ ነዳጅ የሚጠቀም ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ አሌክትሪክ መቀየሩ ተነግሯል።
ሲጀመር የነበረው በቀን የሚቀርበው የውሃ መጠንም ከ20 ሺህ ሜትር ኪዩብ፣በቀን ወደ 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ማደጉም ተነግሯል።
የሚኒስትሩ በሀገር ውስጥ ያለውን ፍላጎት ከማሟላት ስራ ባለፈ እንዲህ አይነቱ ትብብርም ለኢትዮጵያ በጣም ጠቃሚ ነው ብለዋል።

