ኢትዮጵያ በየሳምንቱ ከ90 በላይ ዜጎቿን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እያጣች እንደሆነ ተገለጸ።

በሃገሪቱ በተለይም ካለፈው ሳምንት ወዲህ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

በሃገሪቱ በአሁን ሰዓት በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ጥንቃቄ በጎደላቸው እንቅስቃሴዎች መበራከት ሳቢያ በየሳምንቱ ከ 90 በላይ ሰዎች ህይወት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እያለፈ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዚህ ቫይረስ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎችም በአብዛኛው በሃምሳዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ዜጎች መሆናቸውን በጤና ሚኒስቴር የክሊኒካል ሰርቪስ ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ ሰማን ለ ኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ዜጎች እዴሜያቸው በጣም የገፋ ወይንም ትልቅ የሚባል እንዳልሆነ የሚናገሩት አቶ ያዕቆብ የዚሁ ቫይረስ ሰለባ እየሆኑ ያሉ ዜጎች እራሳቸውንና ቤተሰብን ብሎም ለሃገር ብዙ መስራት የሚችሉ ነገር ግን ይህ ቫይረስ እነዚህን ዜጎች እያሳጣን እንደሆነና ሁኔታው በእጅጉ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ነግረውናል፡፡

ይሄ በሆኑም የተነሳ በአዲስ አበባ የሚገኙ በተለይም ለፅኑ ህክምና የሚረዱ አልጋዎች ሙሉ በሙሉ እየሞሉ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በየእለቱም መንቀሳቀስ የማይችሉ ወይንም በተለያዩ ምክንያቶች ከቤት ውስጥ እንኳን ብዙ ጊዜ የማይወጡ ሰዎች ጭምር በዚሁ ቫይረስ እየተጠቁ መሆኑን ሁኔታውን አሳሳቢ እንዳደረገው ነግረውናል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ከገባ ድፍን አንድ ዓመት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ብቻ የቀሩት ሲሆን ቫይረሱ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 156 ሺህ 112 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል 2 ሺህ 321 ሰዎች ሞተዋል፤ 133 ሺህ 607 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe