የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጅምላ ጨራሽ መሳሪያ ብዜትን እና ይህንኑ በገንዘብ የሚደግፉ ሰዎችን የተመለከተ ክልከላን በህግ ባለማውጣቷ ህጉን ካላፀደቁት ሀገራት ከኢራንና ከመን ጎን መመደቧ ተሰማ፡፡
ይህንኑ አዋጅ በህግ ለማፀደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰሞኑን የቀረበው ረቂቅ አዋጅ እንደሚያመለክተው ከሆነ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ብዜት የሚያደርጉና ይህንኑ በገንዘባቸው የሚደግፉ ሰዎችንና ድርጅቶችን ህገ ወጥ ለማድረግና የሚያንቀሳቅሱትን ሀብት ለማገድ የሚደነግገው አዋጅ በውጭ ሀገር ህገ ወጥነቱ የተጠረጠረ ግለሰብ ወይም ድርጅት በኢትዮጵያ ያለውን ሀብት እንዳያንቀሳቅስ ለማደረግ በመንግስት የሚሰጠው ውሳኔ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
በሰላም ሚኒስቴር ሰብሳቢነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ ሆኖ የሚዋቀረው ኮሚቴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚፈለጉና በሀብትና ንብረታቸው እንዲታገድ ጥያቄ ሲቀርብለት ማንኛወቅም ሰው የጅመላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ብዜትን ወይም እቅድን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በተሟላ ሁኔታም ሆነ በከፊል በገንዘብ በቁሳቁስ፤ በንብረት፤ በኢኮኖሚያዊ ሀብቶች፤ በገንዘብ ነክ አገልግሎቶች ወይም በቴክኒክዊና ሙያዊ አስተዋፅኦ መደገፍ የተከለከለ ነው፡፡ በመሆኑን ይህንን ህግ የሚተላለፉ ሰዎችና ድርጅቶች ላይ የገንዘብ ዝውውሮችን ለመግታት በንብረቱ ወይም ማናቸውም ዋጋ ባላቸው ሀብቶቹ ላይ እግድ ይጥላል፡፡ ገንዘቡ ወይም ሀብቱ ለድርጅቱ ወይም ለእርሱ ወይም በእርሱ ስር ለሚሰሩ ወይም ታዘው ለሚሰሩ ሰዎች ተደራሽ እንዳይሆን የሚከላከል ውሳኔን ያሳልፋል፡፡
ኮሚቴው የሰጠውን የገንዘብ እግድ ወይም የንብረት ዝርውውር ውሳኔ ዝርዝር መረጃ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚታተወም ጋዜጣ ላይ ታትሞ እንዲወጣ የሚያደርግ ሲሆን ባንኮችና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ይህንን መሰረት በማድረግ ንብረቱንና ሀብቱን በማገድ ለኮሚቴው የማሳወቅ ግዴታ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተጥሎባቸዋል፡፡ እግድ ከማይጣልባቸው ሀብቶች መሀከል የዋስትና ክፍያዎች፤በደሞዝ፤ በግብርና በቀረጥ በመድህን አረቦ እንዲሁም በህዝባዊ አጋልግሎት ክፍያዎች ተፈፃሚ እንደማይሆን ተደንግጓል፡፡