ኢትዮጵያ በጤፍ ባለቤትነት ላይ በሄግ ታደረግው የነበረውን ክርክር በአሸናፊነት አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በጤፍ ባለቤትነት ላይ በሄግ ታደረግው የነበረውን ክርክር በአሸናፊነት አጠናቀቀች።

ከአመታት በፊት የጤፍ ዱቄትን አገኘሁ በሚል ከኔዘርላንድ መንግስት የባለቤትነት ፍቃድ የወሰደው ሄልዝ ኤንድ ፐርፎርማንስ ፉድ ኢንተርናሽናል የተባለ የሆላንድ ኩባንያ ነበር።

ኩባንያው ከሆላንድ አልፎ በጣሊያን፣በቤልጄም፣ በኦስትሪያና በእንግሊዝ በጤፍ ላይ የባለቤትነት ፍቃድ ነበረው።
ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ በሄግ ያደረገችው ክርክር ግን ሙሉ የባለቤትነት መብቷን እንድታስመልስ እንዳደረጋት ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩት አምበሳደር ፍፁም አረጋ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።

ፍርድ ቤቱ ባለፈው ህዳር የጤፍ ዱቄት ማግኘት የጤፍ ባለቤትነት መብት አያሰጥም በሚል ሙሉ መብቱን ለኢትዮጵያ ቢሰጥም መዝገቡን እስከ ትላንት ድረስ ለይግባኝ ክፍት እንደነበር ገልፀዋል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን የሰጠው በጤፍ ዱቄት ላይ ምንም ዓይነት የፈጠራ መብት እንደሌለበትና በተልምዷዊ ዝግጅት የሚገኝ በመሆኑ ጭምር ነው ተብሏል፡፡

ሆኖም የኔዘርላድ መንግስት ድጋፍ እንዲሁም በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ የበላቤትነት መብቱን ለማስመለስ የተደረገው ዘመቻ ተፅእኖ ፈጥሮ ሙሉ የባለቤትነት መብቱን ማስመለስ መቻሉን አምባሳደር ፍፁም ገልፀዋል።

Sourceኢብኮ
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe