ኢትዮጵያ በ6 ወራት 976 የሳይበር ጥቃት ሙከራ ተደርጎባታል

ባለፉት ስድስት ወራት 976 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ወደ ኢትዮጵያ ተቋማት መሰንዘራቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ገለፀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው በበጀት ዓመቱ ከወትሮው በተለየ መልኩ በርካታ የሳይበር ጥቃቶች ተሞክረዋል ብለዋል።

የሳይበር ጥቃቱ መብዛት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተላቸው ዲጂታል ለውጦች፣ በትግራይ ክልል የነበረውን የህግ ማስከበር ዘመቻና ሌሎች ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶችን ኢላማ ያደረጉ የሳይበር ጥቃቶች መበራከት  ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የተሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች በ2012 ዓ.ም አጠቃላይ ከተፈፀመው አሃዝ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ዶክተር ሹመቴ ጠቅሰዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ብቻ ወደ ኢትዮጵያ የሳይበር ምህዳር የተሞከሩ ጥቃቶች 976 መሆናቸውን አብራርተዋል።

ከተሰነዘሩት ጥቃቶች መካከል 40 በመቶዎቹ ወደ ፋይናንስ ተቋማት የተሞከሩ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ወደ መንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ መገናኛ ብዙሃን፣ የትምህርት ተቋማትና ሌሎች ቢሮዎች የተደረጉ  መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ለኢዜአ ገልፀዋል።

“በተሰነዘረው የሳይበር ጥቃት የደረሰ ጉዳት የለም ማለት አንችልም” ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የተወሰኑ ድረ-ገፆች መቋረጣቸውን ተናግረዋል።

ተገቢ የሰው ሃይል፣ የቴክኖሎጂና የአሰራር ስርዓት ተዘርግቶ የሳይበር ጥበቃ እየተደረገ በመሆኑ ሙከራው ከሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ አቅም በላይ እንዳልነበር ገልጸዋል።

የሳይበር ጥቃቶቹ ከየት አካባቢ እንደተሰነዘሩ ለማወቅ ጊዜ እንደሚወስድ ገልጸው፤ በታወቀ ጊዜ መንግስት አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ ዶክተር ሹመቴ ገልፀዋል።

Sourceፋና
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe