ኢትዮጵያ ከዩክሬን እንቁላል ለማስገባት ተስማምታለች የተባለው መረጃ መሰረተ ቢስ ነዉ ተባለ

ትዮጵያ ከዩክሬን እንቁላል በመግዛት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ስምምነት ላይ ደርሳለች በሚል በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተላለፈ ያለዉ መረጃ መሰረተ ቢስ ነዉ ሲል የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
————————–
የዩክሬይን የምግብ ደህንነትና የሸማቾች ጥበቃ አገልግሎት በድረ-ገፁ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያና ዩክሬይን መካከል እንቁላልን ለመላክ የሚያስችል የጤና ሰርተፍኬት ለማዘጋጀት ስምምነት ተፈፅሟል፡፡

በመሆኑም አሁን የዩክሬይን እንቁላል አምራቾች ወደ ኢትዮጵያ ምርታቸውን የመላክ ፈቃድ እንዳገኙ ጨምሮ ገልጿል በሚል በተለያየ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የተሰራጨዉ ዜና ፍጹም ከእዉነት የራቀ ነዉ፤ ግብርና ሚኒስቴርም ይሁን ንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር እንቁላል ከዩክሬን ለማስገባት ስምምነት አልፈጸሙም ሲሉ በግብርና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳሬክተር አቶ አበራ ለማ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

የተሰራጨው መረጃ ፍጹም ከእዉነት የራቀ ነዉም ብለዋል፡፡
አቶ አበራ አክለው እንደገለፁት በዶሮ እርባታ የተሰማሩ በርካታ አምራቾች አሉ ሆኖም ምርቱን ለማሳደግ አሁንም አምራቾችን በማበረታታት የዶሮ መኖ ከቀረጥ ነጻ አንዲገባ በማድረግ ረገድ ግብርና ሚኒስቴር እየደገፋቸዉ ይገኛል፡፡ አሐዱ ራዲዮ 94.3

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe