ኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ለሁሉም ዜጎቿ የኮሮና ክትባቶችን መስጠት ጀመረች

እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ እና በየትኛውም የሃገሪቱ አካባቢ የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ክትባቶቹን በነጻ ማግኘት ይችላል ተብሏል፡፡“ዴልታ” የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በኢትዮጵያ መኖሩ መረጋገጡን ተከትሎ የጥንቃቄ እርምጃዎች ይበልጥ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያሳሰቡት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ናቸው ይህን ያሉት፡፡በተሰሩ በርካታ ስራዎች የክትባት ተደራሽነት እየሰፋ እንደሚገኝ የገለጹ ዶ/ር ሊያ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ዜጎች መከተብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሯ “ዴልታ” የተሰኘው ዝርያ በስርጭት ፍጥነት ቀደም ብሎ ከነበረው አልፋ ከተሰኘው ዝርያ በ2 እጥፍ እንደሚበልጥ ተናግረዋል፡፡በመሆኑም ህብረተሰቡ ከመከላከያ መንገዶች ጎን ለጎን የተሳሳቱ አመለካከቶችን በመተው ቫይረሱን ለከላከል፤ ቢያዙም ጽኑ ታማሚ ከመሆን የሚታደገውን ክትባት እንዲያገኝ መክረዋል፡፡በዝግ ቦታዎች የሚደረጉ መሰባሰቦችን መቀነስ እንደሚያስፈልግና አገልግሎት ሰጭ ተቋማትም ጥንቃቄያቸውን መጨመር እንደሚገባቸውም ነው ዶ/ር ሊያ ያሳሰቡት፡፡

ባለፈው ሳምንት ብቻ 8 ሺ 300 ሰዎች በኮሮና መያዛቸውንና 118 ሰዎች መሞታቸውን በዚህም ሳምንታዊ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ 20 ፐርሰንት መድረሱን አማካይ የሞት ምጣኔም በቀን 16 ሰዎች መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 8 ሺ 839 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 1 ሺ 398 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጠቆመው ሚኒስቴሩ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 317 ሺ 572 መድረሱ አስታውቋል።ትናንት ያገገሙትን 606 ሰዎች ጨምሮ በአጠቃላይ እስካሁን 285 ሺ 501 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውንም ገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe