ኢትዮጵያ ከ453 ሺህ በላይ ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ከአሜሪካ ተረከበች

ኢትዮጵያ እስካሁን በአጠቃላይ 3 ሚሊዮን ገደማ ክትባት ወደ ሀገር ውስጥ አስገብታለች።

ዛሬ አዲስ አበባ የገባው የክትባት መጠን አሜሪካ ለኢትዮጵያ ለመስጠት ቃል ከገባችው 1. 2 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት መጠን ላይ ነው።

ኢትዮጵያ ከ453 ሺህ በላይ ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ክትቫት ከአሜሪካ ተረከበች።አሜሪካ ለኢትዮጵያ የለገሰችውን 453 ሺህ 600 ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተረክበዋል።

በአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የተደረገው ድጋፍ “ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን” የተባለው ክትባት ሲሆን ቃል ከገባችው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶዝ 453 ሺህ 600 ዶዙ ዛሬ ረፋድ አዲስ አበባ መግባቱን ኢዜአ ዘግቧል።

የድጋፍ ክትባቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ተረክበዋል።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ ከትባት ለመለገስ ቃል የገባች ሲሆን በዛሬው እለት 453 ሺህ 600 ዶዙን ተረክባለች።

አሜሪካ በሚቀጥሉት ሳምንታት 25 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ለ49 የአፍሪካ አገራት ድጋፍ እንደምታደርግ ታውቋል።

በመጀመሪያው ዙር 1 ሚሊዮን ዶዝ ለቡርኪናፋሶ፣ ለጅቡቲ እና ኢትዮጵያ ተደራሽ ይሆናል።ኢትዮጵያ ቫይረሱን ለመከላከል እስካሁን ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ዜጎች “የአስተራዘኒክ” እና “ሲኖፋርም” የተባሉ ክትባቶችን መስጠቷ ይታወቃል።

በኢትዮጵያ 277 ሺህ 696 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሲሆን 4 ሺህ 357 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን እንዳጡ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe