ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ደረጃ የውሃ ሙሌት ለመጀመር  የግብፅን ይሁንታ እንደማትፈልግ ለፀጥታው ምክር ቤት አሳወቀች።

ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ደረጃ የውሃ ሙሌት ለመጀመር ባለው የህግ ማእቀፍ መሰረት የግብፅን ይሁንታ እንደማትፈልግ ለፀጥታው ምክር ቤት አሳወቀች።

ባለ 22 ገፁ ደብዳቤ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ የተፈረመበት ሲሆን ለምክር ቤቱ ያስገቡት በUN የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ታዬ_አፅቀስላሴ ናቸው። 86 ፐርሰንቱ የናይል ውሃ የሚመነጨው ከሀገሬ ኢትዮጵያ ነው ብለው የሚጀምሩት አቶ ገዱ ግብፅ በኮሎኒያል ስምምነት ላይ ተመስርታ የውሃውን የአንበሳ ድርሻ ስትጠቀም እንደኖረች ተናግረዋል። በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ ውሃውን አመንጭታ ለግብፅ ከማድረስ ባለፈ ለመጠቀም እንዳልቻለች ገልፀው ይህ ኢፍትሃዊነት ሊቀጥል አይችልም ብለዋል። 65 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት የማያገኝ ቢሆንም የግብፅ ህዝብ ግን ባጠቃላይ የአቅርቦት ሽፋን እንደሚያገኝ የሚጠቅሰው ደብዳቤው ግብፅ ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ እንዳናገኝ እንቅፋት መሆኗን ኮንኗል።

Read also:300 አውቶብሶችን ማቆም የሚችለው የቃሊቲ የአውቶብስ ዴፖ ተመርቀ

ኢትዮጵያ ተጨማሪ የማሰቢያ ጊዜ እንደሚያስፈልጋት ገልፃ ባልተሳተፈችበትና በአሜሪካ አደራዳሪነት በተካሄደው የመጨረሻው ውይይት ላይ ያለ ኢትዮጵያ ተሳትፎ ውይይት መደረጉን አቶ ገዱ ለፀጥታው ምክር ቤት አሳውቀዋል። ከዚህ ውይይት በፊት የሚቀሩ አለያይ ነጥቦች (outstanding differences) ነበሩን ብለዋል።

እነሱም በአሜሪካ የቀረበው ረቂቅ ስምምነት

  • የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅምን የሚገድብ መሆኑ
    –  የቀረቡት ህግጋት የግድቡን ቋት በውሃ ለመሙላትና ለመጠቀም የማያስችሉና የተለመዱ አሰራሮችን ያልተከተሉ መሆናቸው
    –  ከህዳሴ ግድብ ውይይት የሰፋ ማእቀፍ ያለው ወይም በግድቡ ላይ ያልተወሰነ መሆኑና የአሁንና የወደፊት ትውልዶችን የመጠቀም መብት የተጋፋ መሆኑ
    –  የኢትዮጵያን በሃብቷ ላይ የማዘዝ ሉአላዊ መብት የተጋፋ መሆኑ እና
    –  ውይይቱ 250 ሚሊዮን ህዝቦችን (Nile riparian countries) ወደ ጎን ትቶ የውሃ ድርሻ ድርድር እንዲሆን መደረጉ
  • Read also:በአረንጓዴ አሻራ ከተከተሉት ችግኞች 84 በመቶ የሚሆኑት መጽደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ…

አቶ ገዱ ግብፅ ቋሚ እንቅፋት መሆኗን አቁማ በትብብር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ማድረግ ይገባታል ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያ የውሃ ሙሌት ለመጀመር ማሰቧ የ Declaration of Principles (DoP) ስምምነትም ሆነ አለም አቀፍ የህግ ሃላፊነትን (international legal obligation) የጣሰ አይደለም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ያቀረበችው የመጀመሪያ ስቴጅ ሙሌት ሁለት አመታት የሚወስድ ሲሆን ከባህር ጠለል በላይ እስከ 595 ሜትር ደረስ የግድቡን ቋት ለመሙላት ያስችላል። ይህም ቋቱ (reservoir) 18.4 billion cubic meter ውሃ እንዲይዝ ያስችለዋል ማለት ነው። ይህ ውሃ የግድቡን ፓወር ፕላንት ለመሞከር ወይም ቴስት ለማድረግ ጥቅም ላይ ይውላል።

Read also:ጤና ሚኒስቴር ስለ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የቀውስ ጊዜ መረጃ አሰጣጥ ፕሮቶኮል…

በመጀመሪያው አመት 4.9 billion cubic meter በሁለተኛው አመት 13.5 billion cubic meter የውሃ ሙሌት ለማካሄድ ታስቧል። ይህ ውሃ የሚወሰደው 49 billion cubic meter አመታዊ ፍሰት ካለው ብሉ ናይል ስለሆነ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ይህ ነው የሚባል ጉዳት (significant harm) አይኖረውም ሲል ደብዳቤው ይገልፃል። በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ሙሌቱን ለመጀመር የግብፅን ይሁንታ ማግኘት እንደማይጠበቅባት እና ህጋዊ ግዴታም እንደሌለባት አሳውቃለች።

Read also:የሕዳሴው ግድብ ዝቅተኛ የመደራደሪያ ነጥባችን የቱጋ ነው?

ኢትዮጵያ ግብፅም ከዚህ በፊት ወደ ነበረው የሶስትዮሽ ውይይት እንድትመለስ ጠይቃለች። ይህ በተዘዋዋሪ በአሜሪካ መሪነት እየተካሄደ ባለው ድርድር ላይ ኢትዮጵያ መቀጠል እንደማትሻ አሳውቃለች።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe