ኢትዮጵያ የበጀት ዓመቱ ሊጠናቀቅ አንድ ወር ሲቀር የ25 ቢሊዮን ብር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሰምምነት አፀደቀች

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን 25.8 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ 15 የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር የሚያስችለውን የስምምነት ፊርማ ዛሬ ከተቋራጮቹ ጋር አድርጓል።

የግንባታው ሙሉ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሽፈን ሲሆን መንገዱን በአማካይ በአራት አመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

Read also:አቶ ስዩም መስፍን የባንክ ሂሳባቸውን ለማስመርመር ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

መንገዶቹን ለመገንባት ጨረታውን አሸንፈው ከባለስልጣኑ ጋር የውል ስምምነት ያደረጉት ተቋራጮች መካከል ሰባቱ ሀገር በቀል ሲሆኑ የተቀረው ደግሞ የውጭ ስራ ተቋራጭ መሆኑ ተገልጿል።

የሚገነቡት መንገዶች በጠቅላላው 1ሺህ 22 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖራቸው በግንባታው ላይ ሰባት የአገር ውስጥና ሌሎች የውጭ አገር ሥራ ተቋራጮች እንደሚሳተፉ ታውቋል።

ከሚገነቡት መንገዶች 13ቱ በአስፋልት ኮንክሪት የሚሰሩ ሲሆን አንድ የጠጠር መንገድ ግንባታና አንድ ከባድ የመንገድ ጥገና ስራ ተካቷል።

Read also:የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከአስር ዓመት በኋላ 2200 በላይ ይደርሳል ተባለ

የግንባታ ሥራዎችም ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር እስከ አራት ዓመት ባለው ጊዜ እንደሚጠናቀቁ ተገልጿል።

የመንገዶቹ ግንባታ በሚጀመርባቸው አካባቢዎች ለማህበረሰቡ የስራ እድል ለመፍጠርና የግብርና ምርቶችን ወደ ገበያ በቀላሉ እንዲደርሱ በማድረግ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል።መንገዶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ባለስልጣኑ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ ገልጿል።

Read also:በጤና ተቋማት የሳይበር ጥቃቶች መጨመራቸዉ ተሰማ

በኢትዮጵያ በየዓመቱ  ሰኔ ሲመጣ በርካታ የመንግስት መስሪሪ ቤቶች ያልተገባ ግዥ በጥድፊያ የሚፈፅሙ ሲሆን መንግስት ሰኔ ከገባ በኋላ ምንም አይነት ግዢ እንዳጥፈፀም የሚከልክል መመሪያ ቢያወጣም በዚህ የፈርማ ስነ ስርዓት ላይ የፖርላማ አባላት ጭምር መገኘታቸው ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe