ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ስድስት ወር 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፤

በጦርነቱ ምክንያት 4 ቢሊዮን ብር አጥቻለሁ አለ፡፡

በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የደንበኞቹን  ብዛት 60.8 ሚልዮን ማድረስ የቻለው ኢትዮ ቴሌኮም  የዕቅዴን 100% ማሳካት ችያለሁ› ማለቱ ተገለፀ፡፡ አፈፃፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ20% እድገት ያሳየ ሲሆን  በአገልግሎት አይነት ሲታይ የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት 58.7 ሚሊዮን፣ የመደበኛ ብሮድባንድ ደንበኞች (Fixed Broadband) 443 ሺህ የመደበኛ ስልክ ደንበኞች 923 ሺህ እንዲሁም የዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 23.8 ሚሊዮን ናቸው፡፡ የቴሌኮም ስርጸት (teledensity) መጠን 58.5% ሆኗል ተብሏል፡፡

 በሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት አጋጥሞ  የነበረውን  የአገልግሎት መስተጓጎል እና የመሠረተ ልማት ውድመት በመቋቋም የ28 ቢሊየን ብር ገቢ በማግኘት የዕቅዱን  86% ማሳካቱን ይፋ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራሰአስፈጻሚ ወ/ሪ ፍሬህይወት ታምሩ ያም ሆኖ በጦርነቱ ምክንያት  የድርጅቱ መሠረተ ልማቶች በመውደማቸው  የ4 ቢሊየን ብር ገቢ አጥተናል ብለዋል ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው ፡፡

Press conference
Press conference

        በዚህ አስቸጋሪ አና ፈታኝ ወቅት ሠራተኞቻችን እና አመራሩ ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ እና ቁርጠኝነት በበርካታ አካባቢዎች የተቋረጡ አገልግሎቶችን በፍጥነት ማስጀመር ተችሏል። በዚህ አጋጣሚ አገልግሎት ተቋርጦ በነበረባቸው  አካባቢዎች የምትገኙ ደንበኞቻችን በትእግስት ስለጠበቃችሁን እናመሰግናለን ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፡፡

የደንበኞች የቴሌኮም አጠቃቀምን ለማሳደግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ያብራሩት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ  የኔትወርክ ማስፋፊያዎችን፣ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያ እንዲሁም የደንበኞችን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ወቅታዊነትን የተላበሱ 23 አዳዲስ እና 19 ነባር የሀገር ውስጥና የዓለም አቀፍ ምርትና አገልግሎቶችን አሻሽሎ ለደንበኞች ማቅረቡንተናግረዋል፤ የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 74.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በማግኘትና የእቅዱን 89.3% በማሳካት የተመዘገበ ነው፡፡ የተመዘገበው ውጤት ፣በሀገራችን በወቅቱ ከነበረው እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ አንጻር ሲታይ የተመዘገበው ውጤት አመርቂ ሊባል የሚችል ነው ብለዋል፡፡

የቴሌብር አገልግሎት ከኢንዱስትሪው ልምድ በተለየ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ13 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን በማፍራት አጠቃላይ የግብይት መጠኑም (Transaction Value) 5.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል ያሉት ወ/ሪት ፍሬህይወት የቴሌብር አገልግሎትን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግና የኩባንያችን አጋሮችም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል እስካሁን ድረስ ከ46 ሺህ በላይ ኤጀንቶችና ከ11 ሺህ በላይ ነጋዴዎች /Merchants/ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በተጨማሪም ከ11 ባንኮች ጋር የኢንቴግሬሽን ሥራ ተጠናቆ ከባንክ ወደ ቴሌብር ገንዘብ ማስተላለፍ የተቻለ ሲሆን ከ8 ባንኮች ጋር ከቴሌብር ወደ ባንክ ዝውውር እንዲቻል ተደርጓል ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe