ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ትርፉን 75 ቢሊዮን ብር የማድረስ እቅድ እንዳለው አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም  በበጀት ዓመቱ ትርፉን 75 ቢሊዮን ብር የማድረስና በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት፤ የደንበኞቹን ቁጥር በአማካይ በ10 በመቶ የማሳደግ እቅድ እንዳለው አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የደንበኞቹ ቁጥር በየዓመቱ በአማካይ በ10 በመቶ ያድጋል የሚል ትንበያ እንዳለው የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ሲያስታወቁ የተቋሙ ገቢም ከ17 እስከ 22 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል የሚል ትንበያ ማስቀመጡን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል።

ፍሬህይወት ይህን ያሉት፤ የሚመሩትን ተቋም የሶስት ዓመት የዕድገት ስትራቴጂ እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ዛሬ ሰኞ መስከረም 16 ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው። ፍሬህይወት በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ “ወድድር ቢኖርም፤ የሰራነው ትንበያ በሶስቱም አመት በደንበኞች ቁጥርም እንደዚሁም በገቢ [ረገድ] በዕድገት የሚጠናቀቅ ነው” ብለዋል።

መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ዛሬ ይፋ ያደረገው የዕድገት ስትራቴጂ “መሪ” የተሰኘ እና ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን ነው። ተቋሙ የዕድገት ስትራቴጂውን ለመጀመሪያ ጊዜ በሚተገብርበት የ2015 በጀት ዓመት፤ የደንበኞቹን ቁጥር 73.5 ሚሊዮን የማድረስ ዕቅድ አለው።

ገቢን ከማሳደግ አኳያ ከተለመደው የቴሌኮም የገቢ ምንጮች በተጨማሪ ሌሎች እሴት የሚጨምሩ አገልግሎቶችን በመጀመር አዳዲስና የተሸሻሉ የሀገር ውስጥና የውጭ አለም አቀፍ አገልግሎቶችን ለገበያ እንደሚያቀርብም ከዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገለፃ ለመረዳት ችሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe