ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው የ2016 በጀት ዓመት 90.5 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ ገቢ ለማግኘት ማቅዴን እውቁልኝ አለ

ኢትዮ ቴሌኮም ‹‹ በተያዘው የ2016 በጀት ዓመት ሶስተኛ የቴሌኮም ኦፕሬተር ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ እንደሚችል ›› ተናገረ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ይህን የተናገረው የ2016 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅዱን ሐምሌ 20 ቀን 2015 ዓ.ም በስራ አስፈፃሚዋ በኩል ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡‹‹ከሦስት ዓመት የመሪ ዕድገት ስትራቴጂ የተቀዳ ነው ›› የተባለለት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ‹‹ በሁሉም ዘርፍ እድገት ለማስመዝገብ ያለመ ነው ›› ተብሎለታል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬሕወት ታምሩ የተቋማቸውን ሪፖርት ሲያቀርቡ እንደተናገሩት ‹‹ ለሁሉም ተቋማት ለማለት በሚስደፍር መልኩ የተቋሙ ስራ አስተዋፅዖ እያበረከተ ›› ይገኛል፡፡የስራ ዕድል መፍጠርን ጨምሮ የሀገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት ላይ አስተዋፅዖ እያደረገ ነው የተባለለት ኢትዮ-ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመትም የያዛቸውን እቅዶች በፍሬሕወት በኩል አብራርቷል፡፡

በዚህም ዕቅዱ ‹‹ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ሊያስመዘግብ እንደሚችል፣ የውጭ ምንዛሬ መሻሻል ሊያሳይ ስለሚችል፣ መንግስት እያራመደ ያለው ዲጂታላይዜሽን እንዲሁም ሶስተኛው ኦፕሬተር ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ይችላል ›› የሚሉት አንኳር ጉዳዮች ላይ መሰረት ማድረጉን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል፡፡‹‹አዳዲስና ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችን ማስፋፊያና ማጠናከሪያ ፕሮጀክቶችን እንደሚተገብር ›› ተቋሙ ገልፆል።

‹‹ ከምሰጠው መደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት በተጨማሪም ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች ላይ በመሰማራት የፋይናንስ አቅሜን ላጠናክር አቅጄያለሁ ›› ብሏል – ኢትዮ-ቴሌኮም። 90.5 ቢሊዮን አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ በማግኘት ከተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት በ19.4 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ ማቀዱንም እወቁልኝ ብሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe