ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌ ብር ቪዛ ካርድን መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት አስጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ቪዛ ካርድን መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት አስጀመረ፤ ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌ ብር ሱፐር አፕ አማካኝነት ቪዛ ካርድን መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት በይፋ አስጀምሯል።
አገልግሎቱን ኢትዮ ቴሌኮም፣ ቪዛ ካርድ እና አቢሲኒያ ባንክ በዛሬው ዕለት በጋራ አስጀምረውታል፡፡ቪዛ ዳይሬክትና ቴሌብር ሬሚት አፕን በቴሌብር ሱፐር አፕ በማውረድ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።
አገልግሎቱ በ190 ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች የቪዛ ዳይሬክትን ተጠቅመው በቀላሉ ብር መላክ እና መቀበል የሚችሉበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ÷ አገልግሎቱ ዜጎች በየትኛውም ሀገር ሆነው የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ገንዘብ የሚልኩበትና የሚቀበሉበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህም ወደ ሀገር ውስጥ የሚላከውን የገንዘብ መጠን (ሬሚታንስ) እንደሚያሳድገው ነው የገለጹት፡፡

የቴሌብር ሬሚት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከአሜሪካ፣ ካናዳ፣ እስራኤል፣ ሳኡዲአረቢያ፣ ዩናይትድ አረብኢምሬትስ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጣሊያን እና ስዊድን ለዚሁ አገልግሎት በኩባንያችን የበለጸገውን ዘመናዊ የቴሌብር ሬሚት መተግበሪያ በመጫን ገንዘብ ለቴሌብር ደንበኞች በቀጥታ መላክ ይችላሉ፡፡
ይህ ስትራቴጂያዊ ስምምነት ከ47.55 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የቴሌብር ደንበኞችን ድንበር ተሻጋሪ እና አስተማማኝ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ጥሬ ገንዘብ የማይጠቀም ማኅበረሰብ (cashless society) በመገንባት የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ ዕውን ለማድረግ የተጀመረውን ጉዞ ለማፋጠን የጎላ ሚና ይኖረዋል።

ደንበኞች የዘመነውን ቴሌብር ሱፐርአፕ ጭነው “VISA” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም በሀገራችን የመጀመሪያው የዋሌት ቨርቿል ቪዛ ካርድ ቁጥር ባለቤት እንዲሆኑ ተጋብዘዋል!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe