ኢትዮ ቴሌኮም በደሴና በኮምቦልቻ የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎት አስጀመረ፤

በኢትዮጵያ ቀዳሚው የቴሌኮምና ዲጂታል አገልግሎቶች አቅራቢው ኢትዮ ቴሌኮም የ5ጂ ኔትወርክ ማስፋፊያ አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በደሴና በኮምቦልቻ ከተሞች አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡
ይህ ኩባንያው  የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን የሚያደርገው ሀገራዊ ጥረት አካል ሲሆን፣ የላቀ ፍጥነት ያለው ኢንተርኔት በማዳረስ ለአዳዲስ ፈጠራዎችና ኢኮኖሚያዊ የዕድገት ዕድሎች በር ለመክፈት ያስችላል።
አገልግሎቱ በደሴ፣ ደሴ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ፣ ሉሲ ሆቴልና ደሴ ሙዚየም አካባቢዎችን ይሸፍናል፡፡
በኮምቦልቻ ደግሞ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ አካባቢዎችን ይሸፍናል፡፡
አገልግሎቱ አዳዲስ የዲጂታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ ለኦንላይን ትምህርት፣ ለጀማሪ የንግድ ተቋማት (startups)፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የዲጂታል ክፍተትን ለማጥበብ፣ የስማርት ስልክ አቅርቦት ለማሳደግና ዲጂታል ክህሎትን ለመጨመር ያስችላል።
5ጂ የግል እና የመንግስት ተቋማትን አሰራር ያዘምናል፤ እንደ ጤና፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ ማኑፋክቸሪንግን፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርት እና ቱሪዝምን የመሳሰሉ ቁልፍ ዘርፎችን በማዘመን ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡
በዚህም ቅልጥፍናን በማሻሻል፣ ምርታማነትን በማሳደግ፣ ወጪዎችን በመቀነስ እና በአዳዲስ ፈጠራ የገቢ እድሎችን በማስፋት ተወዳዳሪ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ያስችላል፡፡
በአዲስ አበባ በ2022 እ.ኤ.አ ያስጀመረገ 5ጂ ደሴ እና ኮምቦልቻን ጨምሮ በ14 ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በጅግጅጋ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በሆሳዕና፣ በአርባ ምንጭ፣ ቢሾፍቱና ጅማ አገልግሎት ላይ ውሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe