ኢትዮ ቴሌኮም “ቴሌብር ሱፐርአፕ” የተሰኘ መተግበሪያ በአዲስ መልክ አበልጽጎ በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀመረ!

በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፤ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በተገኙበት በሳይንስ ሙዚየም ይፋ የተደረገው ቴሌብር ሱፐርአፕ (telebirr Supper App) በዕለት ተዕለት ኑሯቸው የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞችንና አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ ታግዘው ለደንበኞች ለማድረስ የሚሰሩ ቢዝነሶችን ለማገዝና ለማሳለጥ ታስቦ የበለጸገ መተግበሪያ እንደሆነ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል፤

መተግበሪያው እንደ የቴሌብር የፋይናንሻል አገልግሎት፣ ኢ-ኮሜርስ እና አነስተኛ መተግበሪያዎችን (mini-Apps) እንዲሁም ሶሻል ኔትዎርኪንግ እና የህይወት ዘይቤ (Social networking & Lifestyle) የመሳሰሉ አገልግሎቶችን በማቅረብ ደንበኞች በአንድ ጊዜ ፈርጀብዙ የዲጂታል ግብይትአገልግሎቶችን እንዲያገኙ እንዲሁም ለማንኛውም የግዢ ሂደት እንዲጠቀሙ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል፡፡

ይህ አዲሱ መተግበሪያ አሁን በሥራ ላይ ካለው የቴሌብር መተግበሪያ ጋር ተያይዞ የሚታዩ የአፈጻጸም፣ የሴኩሪቲ ሲስተም፣ ወደ ሲስተም ማስገቢያና ምዝገባ ጊዜ (login & registration time) ፣ የተለያዩ መተግበሪያዎችን በማውረድ የስልክ የዳታ የመያዝ አቅም መቀነስ (phone memory consumptions) እና የመሳሰሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችልና የባዮሜትሪክ ማረጋገጫ (biometric authentication)፣ ማይኢትዮቴል መተግበሪያ እና የሌሎች የአጋሮችን መተግበሪያዎችን በማካተት ደንበኞች ወጥ፣ የተቀናጀ፣ ብቁ እንዲሁም የተለያዩ ምርትና አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል እና በአንድ ጊዜ ለደንበኞች ፈርጀብዙ የዲጂታል ግብይት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መተግበሪያ ነው፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች አዲሱን የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ለመጠቀም በቀላሉ ፕሌይ ስቶር ፣ አፕ ስቶር እና አፕ ጋለሪ ላይ በመግባት፣ ነባሩን የቴሌብር መተግበሪያ አሻሽል (update)የሚለውን በመጫን የቴሌብር ሱፐር አፕን በቀላሉ አውርደው መጠቀም ይችላሉ ተብሏል፡፡

የቴሌብር ተጠቃሚዎች እና ሲስተማቸውን ከቴሌብር ጋር በማስተሳሰር የሀገራችንን የዲጅታል ኢኮኖሚ ለመገንባትና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት እየደገፉ ያሉ ደንበኞቻችን፣ የቢዝነስ አጋሮቻችንን፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የንግድ ድርጅቶች፣ አገልግሎት ሰጭ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን እናመሰግናለን ያሉት ወ/ሪት ፍሬሕይወት በጠቃላይ በኢኮሲስተሙ ሚና ያላቸው ባለድርሻ አካላት በቀጣይም ሲስተማቸውን እንዲሁም መተግበሪያቸውን ከቴሌብር ሱፐርአፕ ጋር በማስተሳሰር አብረውን እንዲሰሩና በጋራ የሞባይል ቴክኖሎጂን ጥቅም አሟው በመጠቀም ሀብትና የስራ ዕድል እንድንፈጥር በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe