ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሸን ባንክ ጋር በመሆን ያለ ተያዥ ብድር ሊሰጥ ነው

“የፋይናንስ አገልግሎት ለሁሉም” በሚል ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር አገልግሎቶቹን ይዞ መቅረቡን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።ከመደበኛ ፋይናንስ በተለየ ለድሀው ማህበረሰብ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ይዞ መምጣቱን ነው ይፋ ያደረገው።

ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ አግኝተው ወደ ስራ የገቡት እነዚህ የፋይናንሻል አገልግሎቶች፣ ቴሌብር መላ፤ ቴሌብር እንደኪሴ እና ቴሌብር ሳንዱቅ ናቸው።ሶስቱም የተለያየ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን ይህም የብድር ፣ ኦቨርድራፍት እና ቁጠባ መሆናቸዉ ተነግሯል።

ቴሌ ብር መላ ለግለሰቦችም ለንግድ ተቋማትም የሚቀርብ አገልግሎት ሲሆን፣ደንበኞቹ ባንቀሳቀሱት የገንዘብ ዝውውር መሰረት ታይቶ እስከ 2,000 በወር ደግሞ እስከ 10,000 ብር የሚደርስ ብድር የሚያመቻች አገልግሎት ነው።ለግለሰብ እስከ 10ሺህ ብር በቀን ፣በሳምንት እና በወር ብድር አመቻችቷል።ለዚህም የብድር አገልግሎት ምንም አይነት ተያዥ አያስፈልገውም ነዉ የተባለዉ።

ቴሌ ብር እንደኪሴ በቴሌብር አማካኝነት ግብይት በሚፈጸምበት ጊዜ የቴሌብር ሂሳብ ከሚገዙት እቃ በታች ከሆነ ቀሪውን ክፍያ ጨምሮ ለሻጭ በመክፈል ገንዘብ ገቢ በሚደረግበት ጊዜ ከሂሳብ ላይ ተቀናሽ በማድረግ አገልግሎት ይሰጣል።እስከ ሁለት ሺህ ብር ድረስ ክፍያ መፈፀምም የሚቻልበት ነው።የውሃ ፣መብራት ፣ነዳጅ እና ሌሎች ክፍያዎችን መፈፀም ይቻላል።

ቴሌብር ሳንዱቅ ቴሌብር ላይ ካለው የገንዘብ መጠን ላይ መቆጠብ የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን በሁለት አማራጮች በወለድና ያለወለድ የቀረበ ነው።የወለድ መጠኑም በቀን 7 በመቶ የሚሰላ አመታዊ ወለድ ነው።በቴሌብር መላ 9.8 ቢሊየን ፣በቴሌብር እንደኪሴ 6.4 እና በቴሌብር ሳንዱቅ 3.3 ቢሊየን ብር በአመት ብድር ይሰጣል ተብሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe