ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ሽልማት የሚያስገኙ የኢትዮ 130 ሽልማትን ይፋ አደረገ

“ገቢዬን 163 ቢሊዮን ብር በላይ ለማድረስ እየሠራሁ ነው” ብላል

ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞቹን ቁጥር 83 ሚሊዮን በማድረስ ገቢውን 163 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለማድረስ አቅዶ እየሠራ መኾኑን ገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ዛሬ በስካይላይት ሆቴል በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢውን 163 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዷል።

ለዚህም የደበኞችን ቁጥር አሁን ካለበት ከ78 ሚሊዮን ወደ 83 ሚሊዮን፤ የቴሌብር ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ47 ነጥብ 5 ሚሊዮን ወደ 55 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱን ነው ዋና ሥራ አሥፈጻሚዋ የተናገሩት።

Ethioteleco Prize

የዲጅታል ኢትዮጵያ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ አስተማማኝ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲኾን እየተሠራ ነው ያሉት ዋና ሥራ አሥፈጻሚዋ በበጀት ዓመቱ በ500 ከተሞች 4ጂ እና በ15 ከተሞች 5ጂ የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ ይደረጋል ብለዋል።

ከ1 ሺህ 200 በላይ አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች በዚህ ዓመት እንደሚገነቡም ጠቁመዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በ 15 ከተሞች የ 5ተኛ ትውልድ ኔትዎርክ እና የ 4G አገልግሎት ያላገኙ አካባቢዎች እገልግሎቱን እንዲያገኙ ትኩረት እንደሚደረግ ነው ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ የገለፁት::

ኩባንያው በ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱም የሚታወስ ነው። በዚህ ዓመት 282 ነጥብ 85 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬን ለማስገኘት መታቀዱም ተገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ሀገርን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ግንባታ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አስታወቀ::

የሀገርን የኢኮኖሚ እድገት እና የልማት እንቅስቃሴ ለመደገፍ የቴሌኮም ዘርፍ ትልቅ ሚና እንዳለው የገለፁት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በ2017 በጀት ዓመት ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት ለማስፋፋት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል::

በዚህ አመት 130ኛ አመት የምስረታ በአሉን የሚያከብረው ኢትዮ ቴሌኮም ገቢውን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግም ለደንበኞች ከፍተኛ ሽልማት የሚያስገኙ የአገልግሎት አይነቶችን በማቅረብ ተጠቃሚ ለማድረግ መዘጋጀቱ ይፋ ሆኗል፡፡

በዚህ የሽልማት መርሃ ግብር ላይ ቴሌ ብርን ጨምሮ የኢትዮ ቴሌኮምን ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ለሚጠቀሙ ደንበኞች በመጪዎቹ ስድስት ወራት 6 የኤሌትሪክ አውቶሞቢሎች፤ 9 ባጃጅ፤ክ160 እላይ ስማርት ስልኮችን ጨምሮ ከ260 ሺ በላይ ፓኬጆችን ያካተተ ሽልማቶች መዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe