ኢትዮ ቴሌኮም የሁለት ቢ.ዋይ.ዲ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እና አንድ ባለ 3 እግር ተሽከርካሪን ዕጣ ለባለእድለኞች ያወጣ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ዕጣ ለወጣላቸው ሁለት የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች እድለኞች ቁልፍ አስረክቧል፡፡
ኩባንያችን 130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለደንበኞች ባዘጋጀው የኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ እና ኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ሽልማት መርሃግብር ልዩ ልዩ ሽልማቶችን እያበረከተ ይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለትም በኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ መርሃ ግብር ለእጣው ብቁ ለሆኑ 632,382 ልዩ ደንበኞች አንድ ቢ.ዋይ.ዲ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና እንዲሁም ለእጣው ብቁ ለሆኑ 246,905 ደንበኞች አንድ ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ ዕጣን ለእድለኞች አውጥቷል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ሽልማት መርሃግብር ለእጣው ብቁ ለሆኑ 179,308 ደንበኞች አንድ ቢ.ዋይ.ዲ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ዕጣ ለእድለኞች አውጥቷል፡፡
ባለፉት ሁለት ወራት 57 ዘመናዊ ስማርት ስልኮችን፣ በየቀኑ እና በየሳምንቱ በድምሩ 4.8 ሚሊዮን ብር የቴሌብር ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ እንዲሁም 336,557 የሞባይል ጥቅሎችን በአጠቃላይ ዛሬ የሚወጡትን ሽልማቶች ሳያካትት ከ 14.34 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ሽልማቶች አበርክቷል፡፡
መርሃ ግብሩ አራት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እና ስድስት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ለባለእድለኞች በየቀኑ እና በየሳምንቱ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን እያበረከተ በቀጣይ አራት ተከታታይ ወራት የሚዘልቅ ይሆናል፡፡

