ኢትዮ ቴሌኮም የሚዲያ ስነ-ምህዳሩን የሚያዘምን የ“ቴሌስትሪም” አገልግሎትን በይፋ አስጀመረ

ኩባንያው የሚዲያ ስነ-ምህዳሩን የሚያዘምን አዲስ የ“ቴሌስትሪም” አገልግሎትና የመደበኛ ብሮድባንድ (ዋይ ፋይ) አገልግሎትን የሚያዘምን “ንክኪ-አልባ ዲጂታል አሰራር” በዛሬው ዕለት በይፋ በሳይንስ ሙዚየም አስጀምሯል፡፡
ቴሌስትሪም በኩባንያው የፋይበርና የቴሌ ክላውድ መሰረተ ልማት የሚቀርብ በመሆኑ ተጠቃሚዎች እስከ 4K የሚደርስ የምስል ጥራት ያላቸውን ይዘቶች በማንኛውም የአየር ሁኔታ ያለ መቆራረጥ እንዲመለከቱ ያስችላል ብለዋል የኩባንያው ዋና ስራአስፈታሚ ፍሬህይወት ታምሩ።
አገልግሎቱ ስማርት ያልሆኑ ቴሌቪዥኖችን ወደ ስማርትነት በመቀየር ዘመናዊ የስትሪሚንግ አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ፈር ቀዳጅ አገልግሎት ነው፡፡
ይህ ፕላትፎርም የሀገራችንን ባህል፣ እሴትና ስነ-ምግባር መሰረት ያደረጉ ይዘቶችን የሚያቀርብ ሲሆን፤ የወላጆች ቁጥጥር ሥርዓት መካተቱ አስተማማኝና ተመራጭ ያደርገዋል።
ቴሌስትሪም የሚዲያ ተቋማት ለሳተላይት ኪራይ የሚከፍሉትን የውጭ ምንዛሬ የሚያስቀር ሲሆን፤ ለፊልም ፕሮዲውሰሮች፣ ይዘት ፈጣሪዎች፣ ለትምህርት እና ለቢዝነስ ተቋማት አዲስ አማራጭ ይፈጥራል ተብላል፡፡
በተጨማሪም ኩባንያው የመደበኛ ብሮድባንድ አገልግሎት በማዘመን የደንበኞቻችንን ተሞክሮ በእጅጉ የሚያሻሽል የዲጂታል ሲስተም ተግባራዊ ተደርጓል።
ይህም ደንበኞች ካሉበት ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ ውስጥ በሚገኝ ሚኒ-መተግበሪያ አዲስ ዋይፋይ እንዲጠይቁ ወይም የብልሽት ምዝገባ እንዲያከናውኑ ያስችላል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe