ኢትዮ ቴሌኮም የሰነድ ማረጋገጥና የውክልና አገልግሎትን ዲጂታል የሚያደርገውን “ቴሌሳይን” በይፋ አስመረቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከፍትህ ሚኒስቴር እና ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በመተባበር “ቴሌሳይን” የተሰኘ አዲስ የዲጂታል ሶሉሽን በዛሬው ዕለት በይፋ አስመርቋል።
ይህ ቴክኖሎጂ ዜጎችና የዲያስፖራ ማህበረሰብ በአካል መገኘት ሳያስፈልጋቸው የውክልና ስልጣን መስጠትና ማንሳት፣ የሰነድ ማረጋገጥ እንዲሁም የጠበቃ ፈቃድ ማውጣትና ማደስ እንዲችሉ ያደርጋል።
አዲሱ አሠራር በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የታገዘ በመሆኑ ከፍተኛ ደህንነት ያለው ሲሆን፣ ቀደም ሲል ሳምንታትን ይፈጅ የነበረውን አገልግሎት ወደ ጥቂት ደቂቃዎች ዝቅ አድርጎታል።
ተገልጋዮች ክፍያዎችን በቴሌብር በመፈጸም አገልግሎቱን በሳምንት 7 ቀን፣ በቀን 24 ሰዓት በሞባይል መተግበሪያና በድረ-ገጽ ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
ይህ አገልግሎት በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የመረጃ ሉዓላዊነትን በሚያረጋግጥ መልኩ መረጃዎች በሀገር ውስጥ በሚገኝ የክላውድ መሰረተ-ልማት ላይ እንደሚቀመጡ ታውቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe