ኢትዮ ቴሌኮም የስማርት ባህር ዳር ፕሮጀክት ለመተግበር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጋር ተፈራረመ

ስምምነቱ በምዕራፍ ተከፋፍሎ የሚከናወን ሲሆን የክላውድ፣ ጥሪ ማዕከል፣ ዳታ ሴንተር፣ ባለ ከፍተኛ አቅም ኢንተርኔት፣ የፋይበር መስመር እና ተያያዥ የዲጂታል መሰረተ ልማት በመዘርጋት እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣ ትራንስፖርት፣ ቱሪዝም ያሉ ዘርፎችን ‘ስማርት’ ከማድረግ ባሻገር ደህንነቷ አስተማማኝ የሆነ ከተማ እውን ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
የስማርት ባህር ዳር ፕሮጀክቱ የከተማ አስተዳደሩን ቢሮዎች በዲጂታል ሶሉሽኖች በማስታጠቅ እንዲሁም ክፍያዎችን በቴሌብር በማስተሳሰር የማስፈጸም አቅማቸውን እና ውጤታማነታቸውን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ያስችላል፡፡
ይህም ተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት እንዲችሉ በማገዝ፣ እንግልትን በመቀነስ ህይወታቸውን ለማቅለል እና የአኗኗር ዘይቤያቸውን ለመቀየር ያስችላል፡፡
የፕሮጀክቱ ትግበራ ከተማዋን ለቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት መዳረሻነት ምቹና ተመራጭ በማድረግ ተወዳዳሪነትን የሚጨምር ሲሆን የቢዝነስ እንቅስቃሴ በማሳለጥ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ያሻሽላል፡፡
(ኢትዮ ቴሌኮም)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe