ኢትዮ ኢትዮ ቴሌኮም ሼር ለገዙ ባለአክሲዮን ባለቤቶች የ3 . 5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ለማካፈል ማቀዱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ለ2018 በጀት ዓመት ባወጣው ዕቅድ፣ አጠቃላይ የገቢ መጠኑን 235.8 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ማቀዱን ይፋ  ሲያደርግ ዓመታዊ የተጣራ ትርፉን 35 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር  እንደሚሆን ይፋ አድርጓል። በዚህም አስር ክመቶ ድርሽ የገዙ ባለአክሲዮን ደንበኞች 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ትርፍ እንድሚያግኙ ታውቀል፡፡

ይህ ዕቅድ ካለፈው ዓመት ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ45.6% ከፍተኛ ዕድገት ያሳያል።

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንዳብራሩት፣ በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ትልቁን የገቢ ድርሻ የሚይዘው የዳታና የኢንተርኔት አገልግሎት ሲሆን፣ 23.8% ድርሻ ይኖረዋል። በመቀጠልም የድምፅ አገልግሎት 23.2% ድርሻ ይይዛል።

በተጨማሪ፣ እንደ ኢንተርፕራይዝ አገልግሎቶች (10.2%), የተጨማሪ እሴት አገልግሎቶች (VAS) (7.6%), እና ቴሌብር (3.6%) ያሉ አዳዲስ የንግድ ዘርፎች ለኩባንያው ገቢ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ተብሎ ታቅዷል።

ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብርን አገልግሎት ለማስፋፋትና ለማጠናከር ሰፊ ዕቅድ ያወጣ ሲሆን፣ በዚህም የቴሌብር ተጠቃሚዎች ቁጥር በ14% በማደግ 62.5 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ከቴሌብር የሚገኘው ገቢ በ93.9% በማደግ ወደ 8.5 ቢሊዮን ብር ያድጋል ተብሎ ተጠብቋል። በተጨማሪም የግብይት መጠኑ በ86% ወደ 4.43 ትሪሊዮን ብር፣ እንዲሁም የግብይት ብዛቱ በ83% በማደግ ወደ 1.94 ቢሊዮን ለማድረስ ታቅዷል።

ከዚህ በተጨማሪ በተያዘው በጀት ዓመት ኢትዮቴሌኮም ከ235 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አቀዳል።የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የቀጣይ የሶስትና የአንድ ዓመት ስትራቴጂካዊ እቅድን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፤ ኢትዮ ቴሌኮም በ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢውን 235 ነጦብ 8 ቢሊዮን ብር ለማድረስ አቅዷል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ ለማግኘት የታቀደው እቅድ ከ2017 ዓ. ም በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ45 ነጥብ 6 በመቶ ጭማሪ አለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ለማግኘት ከታቀደው ገቢ ውስጥ የቴሌኮም አገልግሎት ትልቁን ድርሻ ይይዛል፤ ከዚህም አገልግሎት 133 ቢሊዮን ብር ገቢን ለማግኘት አቅዷል ያሉት ስራ አስፈጻሚዋ፤ ወደ 40 መቶ የሚጠጋ ገቢውንም ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት ባሻገር ካሉ የቢዝነስ ሥራዎች ለማግኘት ይሰራል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የዳታ እና የኢንተርኔት አገልግሎት 23 ነጥብ 8 በመቶ፤ የድምፅ አገልግሎት 23 ነጥብ 2 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ጠቁመዋል።
የደንበኞችን ቁጥር 88 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱን ገልጸው፤ እቅዱን እውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራ ይሰራል ብለዋል።
ከዚህ ሌላ ኢትዮ ቴሌኮም በቀጣይ ሶስት አመታት የሚመራበትን አዲስ ስትራቴጂን ይፍ አደረገ ።
“የቀጣይ አድማስ” (Next Horizon) የሚል  መሪ ቃል ያለው ይህ የሶስት አመታት ስትራቴጂ፣ ተቋሙን ከቀላል የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪነት ወደ ዘመናዊና ሁለገብ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ከፍ የሚያደርግ ነው።
“Next Hotzone Beyond Digital” በሚል ጽንሰ ሀሳብ ላይ የተመሰረተው ይህ አዲስ ስትራቴጂ፣ የኢትዮጵያን የዲጂታል ለውጥ እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ። በርካታ ሀገራዊ ዕቅዶችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ሲሆን፣ በተለይም የመንግስትን የ10 ዓመት የልማት እቅድ እና የኢትዮጵያን የዲጂታል ስትራቴጂ ለማላቅም ያስችላል ብለዋል።
ይህ አዲስ ስትራቴጂ የኢንዱስትሪውን የእድገት ማማ ለማላቅ እና ከአህጉራዊም ሆነ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ውስጥ በመግባት  የገበያ አድማሱን ለማስፋት የሚያስችል ነው ብለዋል። ኢትዮ ቴሌኮም ከቴሌኮም አገልግሎት ባሻገር፣ ሌሎች መልከ ብዙ የዲጂታል አገልግሎቶችን በማቅረብ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ልህቀት አስተዋጽኦ ያደርጋል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe