ኢንሹራንስ እና ባንኮች የልማት ባንክ ቦንድ እንዲገዙ ተወሰነ!

ኢንሹራንሶች ከአመታዊ ገቢያቸው 15% የልማት ባንክ ቦንድ እንዲገዙ ተወሰነ።ውሳኔው ከነሃሴ 26 ጀምሮ ይተገበራል።ባንኮች ከጠቅላላ አመታዊ የብድር ክምችት 1% የልማት ባንክ ቦንድ መግዛት ይጀምራሉ።

የባንኮች መጠባበቂያ መጠን ከጠቅላላው ተቀማጭ 10% እንዲሆን ተወሰነ።ቀደም ሲል 5% እንደነበር ይታወሳል።ከወጪ ንግድ፣ ከግለሰብ ሃዋላ እና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች የሚገኝ የውጭ ምንዛሬ 50% ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ይደረጋል። ቀደም ሲል 40% በመቶ ነበር።የውጭ ምንዛሬ ያስገኘ ደንበኛ ያለገደብ የሚቀመጥለት የውጭ ምንዛሬ መቶኛ 40% እንዲሆን ተወስኗል።ይህ መጠን 31.5% ነበር።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe