ኢጋድ የኮቪድ 19 ወረርሽንን ለመከላከል 25 ሺህ ዶላር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገ

የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ የኮቪድ 19 ወረርሽንን ለመከላከል 25 ሺህ ዶላር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገ፡፡
የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት ድርጅት ኢጋድ ኢትዮጲያን ጨምሮ 8 የአፍሪካ ሀገሮችን በስሩ የያዘ ሲሆን የነኝህን ሀገሮች ላይ የሰላም ፀጥታ፤ የጤና ፕሮግራም ፤በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች ላይ ሀገሮችን በማስተባበር ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ድርጅት ነዉ፡፡

Read also:ኢትዮጵያ ለኮረና ቫይረስ ፈውስ የሚሆኑ 45 ባህላዊ መድሃኒቶች ላይ ሳይንሳዊ ምርምር…

ድርጅቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ስጋት የሆነዉ ኮቪድ 19 ወረርሽንን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ 25 ሽህ ዶላር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የኢጋድ ሲኔር አማካሪ እና የኮቪድ 19 የኢትዮጵያ ተጠሪ ዶ/ር ግሩም ሀይሉ ሀገራቱ በተስማሙበት ዉሳኔ መሰረት ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እየሰራች ያለውን ስራ ለመደገፍ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

Read also:ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ደረጃ የውሃ ሙሌት ለመጀመር  የግብፅን ይሁንታ እንደማትፈልግ ለፀጥታው ምክር…

ድጋፉን የተረከቡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ኢጋድ ያደረገውን የመከላከያ ቁሳቁሶች ድጋፍ የቫይረስ ወረርሽኙን ለመከላከል በድንበር አካባቢ ለሚሰሩ ስራዎች፡በስደተኛ ካፕ ለሚገኑ እና ለተፈናቃዮች ጥቅም ላይ ይዉላሉ ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሊያ አክለው ኢጋድ ያደረገው ድጋፍ ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እየሰራች ያለውን ስራ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe