እስራኤል በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣዉን የዉስጥ ግጭት በመንተራስ የኢምግሬሽን ፖሊሲዋን ልትገመግም ነዉ

እስራኤል በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣዉን የዉስጥ ግጭት በመንተራስ ቤተእስራኤላውያን የምታሶጣበትን የኢምግሬሽን ፖሊሲዋን ልትገመግም ነዉ ተባለ!

እስራኤል በኢትዮጵያ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተእስራኤላውያንን የምታጓጉዝበትን ፖሊሲ ልትገመግም እንደሆነ ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል። ሀገሪቱ ለዚህ እንደምክንያት ያስቀመጠችዉ ደግሞ በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣዉን የዉስጥ ግጭት መበራከት ነዉ።

ባሳለፍነዉ ሳምንት በእስራኤል የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በእየሩሳሌም ከተማ በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው በአፋጣኝ ከግጭት ቀጠናዎች እንዲወጡ እና ወደ ሀገሪቱ እንዲጓጓዙ በመጠየቅ ሰልፍ ማድረጋቸዉን ብስራት ራዲዮ እና ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወሳል። ሰልፈኞቹን እንዲበተኑ በተደረገ ጥረትም ከሀገሪቱ ፖሊሶች ግጭት ዉስጥ መግባታቸዉ አይዘነጋም።

ከዚህ ሰልፍ በኋላም የኢሚግሬሽን እና ስደተኛ ተቀባይ ሚኒስትሩ ኦፊር ሶፈር ፤ በሀገሪቱ የስደተኞች ፖሊሲ ላይ የግምገማ ሂደቱን የሚከታተሉ ባለሙያ መመደባቸዉ ተሰምቷል። እስራኤል በቅርቡ 204 ቤተ እስራኤላውያን እና ዜጎቿን ከጎንደር እና ግጭት ከነበረባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ማስወጣቷ ይታወሳል።

ሚኒስትሩ ለዚህ ዉሳኔ የበቁት ፤ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡትን የቤተእስራኤላውያን ቁጥር ለመጨመር ከሚሰሩ ማህበረሰብ እንቂዎች ጋር ከተቃዉሞ ሰልፉ በኋላ ካደረጉት ንግግር በኋላ እንደሆነ ተገልጿል።

✍️ዳጉ ጆርናል
@YeneTube

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe