እስራኤል በጋዛ እያደረገችው ባለው ጦርነት ወዳጅ አገራት ከእስራኤል ፍላጎት ውጪ ያለውን ውሳኔ ወሰኑ

የጋዛው ጦርነት ሁለት ዓመት ደፍኗል። በእነዚህ ጊዚያት ውስጥ በአስርሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ተገድለዋል፤50 የሚሆኑ ታጋቾች እስካሁን በሃማስ ተይዘዋል።
ይህን መቋጫ ያጣውን ጦርነት ለማስቆም የእስራኤል አጋር የሆኑ አገራት የሁለት መንግስታት መመስረትን እንደምርጫ አድርገው ወስደውታል። እናም ለፍልስጤም የአገርነት እውቅና ሰጥተዋል። በርግጥ እስራኤል በድርጊቱ ብትከፋም።
በዚህ ስዓት ከ150 በላይ አገራት ለፍልስጤም የአገርነት እውቅና ሰጥተዋል። እስራኤል በጋዛ እያደረገችው ባለው ጦርነት ያልተደሰቱና የተቃወሙ የእስራኤል ወዳጅ አገራት ከእስራኤል ፍላጎት ውጪ ያለውን ውሳኔ ወስነዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኔትንያሁም ድርጊቱ ሽብርን መሸለም ሲሉ ጠርተውታል።
ይህ የአገራቱ እውቅና በመሬት የሚለውጠው ነገር ምንም እንደሌለ ነው እየተገለፀ ያለው። የእስራኤል ጦር በጋዛ ማጥቃቱን እንደገፋበት ነው እናም የለወጠው አንዳች ነገር የለም እየተባለ ነው።
ፍልስጤማዊያኑም ቢሆን የአገራቱ እውቅና በጋዛ ያለውን ነገር ከመለወጥ አኳያ ምንም ነው፤የእኛ ተስፋ ፈጣሪ ጦርነቱን እንዲያስቆመው ብቻ ነው በማለት ላይ ናቸው።
ይህ የአራቱ እውቅና ፕለቲካሊ የሚለውጠው ነገር ምንምድን ነው የሚለውን ስንመለከት ፍልስጤምን የመንግስታቱ ድርጅት ቋሚ አባልነትንም የሚያሰጥ አይደለም።
የድርጅቱ ሙሉ አባልነት በጸጥታው ምክር ቤት እውቅና እስካልተሰጠው ድረስ መሆን አይቻልም ይህን ደግሞ አሜሪካ በፍጹም የምትፈቅደው ጉዳይ አይደለም።
በርግጥ ይህ እውቅና ለፍልስጤማዊያን ቀላል ትርጉም ባይኖረውም፤መሬት ላይ ያለውን ሀቅ ግን አይለውጠውም የሚሉ ተንታኞች ብዙ ናቸው። እስራኤል ደግሞ ከፍልስጤም ወዳጅ ባልሆኑ አገራት ጭምር የሚደርስባት ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዲበረታባት አድርጓል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትላንት በድርጅቱ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ሁላችሁም እንደምታውቁት በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥረት አድርጊያለሁ፤የሚያሳዝነው ግን ሀማስ በተደጋጋሚ ባለመቀበሉ ሳይሳካ ቀርቷል ብለዋል።
ኦክቶበር 7ንም በፍጹም ልንረሳው አንችልም ብለዋል። ኦክቶበር 7 ሃማስ በድንገት በእስራኤል ላይ ጥቃት የከፈትበትና የጋዛውም ጦርነት እንዲጀመር ምክንያት የሆነ አጋጣሚ ነው።
እናም አሁን አንዳንድ አገራት ለፍልስጤም እውቅና በመስጠት ጦርነቱ እንዲቀጥል ድጋፍ እያደረጉ ነው፤ለሃማስም የማይገባውን እውቅና እየሰጡ ነው ብለዋል።
አሁን ለሃማስ አንድ መልዕክት አለኝ ታጋቾችን አሁን ልቀቁ ሲሉም ቆፍጠን ያለ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
እስራኤል ዩኬ፣ ፈረንሳይ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ እንዲሁም ሌሎች አገራት ለፍልስጤም እውቅና መስጠታቸውን ጨምሮ የተመድን ስብሰባ የተመለከተችውም አገሪቷ ላይ ጥቃት የመፈፀመውን እና በርካቶችን አግቶ የወሰደውን ሐማስ እንደመሸለም ነው።
አንዳንድ የእስራኤል ሚኒስትሮችም ለዚህ ምላሹ መሆን ያለበት የፍልስጤም ግዛት እስከወዲያኛው እንዳይኖር ማድረግ እና በእስራኤል ሥር የምትገኘው ዌስት ባንክ ከእስራኤል ጋር መጠቅለሏን ማወጅ እንዲሆን ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe